ሁሉንም ነገር ለመልካም ይሆናል

ሁሉንም ነገር ለመልካም ይሆናል

እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን፡፡ ሮሜ 8 28

እግዚአብሔር ሲናገረን የምንታዘዘው በእምነት ነው፡፡ በገሃድ ዓለም ምንም ዓይነት ትክክል ለማድረጋችንና ትክክል ላለማድረጋችን የምናረጋግጥበት ሁኔታ የለም፡፡ ይሄ እምነት የሚሠራበት መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መከተላችን በምንወስደው የእምነት እርምጃ እንጅ በተፈጥሮ ሕዋሳችን በኩል አይደለም የምናረጋግጠው፡፡ የእርሱን ድምፅ በእምነት ተቀብለን መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ከጌታ ጋር ያለን ልምምድ ትልቅ አስተማሪ ነው፡፡ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ትክክል እንሁን ወይም ትክክል አንሁን በእምነት እርምጃ በመውሰድ ውጤቱን በማየት ካልሆነ ሌላ የምናውቅበት መንገድ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ልንሳሳት እንችላለን፡፡ ስህተትም ሰርተን በሃሣብ ልንጨነቅ እንችላለን፡፡ ብዙውን ጊዜ እናስባለን፡፡ ሰርቼ ከመሳሳት መቆጠብ ይሻለኛል እንላለን፡፡ ነገር ግን እንደዚያ ካደረግን በኋላ እግዚብሔር በእርግጥ ሲናረን ደግሞ ወዲያው ሕይወታችን ይዘበራረቃል፣ የሕይወታችን መዘበራረቅ ብቻ ሳይሆን የጭንቀትና ውጤት አልባ ሕይወት የድል ሕይወት እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ፍርሃት የእርሱን ደስታ እንዳናውቅ ይከለክለናል፡፡ በሕይወቴ የተለማመድኩት ልባችን በትክክለኛ መንገድ መንገድ ላይ ሲሆን ስሆን ከእግዚአብሔር ለመስማት በምንማርበት መንገድ ላይ የምናውቀውን መልካሙን ነገር ስናደርግ እርሱ የእኛን ጥረትና የመታዘዝ እርምጃችንን ያከብራል፡፡ እኛ እንደ ሕፃናት ዓይነት መታመን ይዘን የሰማነውን ለመታዘዝ በልባችን ስናምን እርሱ እንደሚያደርገው ነግሮናል፡፡ ምንም እንኳ ሁሉን ነገር በትክክል ብናደርገውም፡፡ እግዚአብሔር ስህተታችንን ለመልካም እንዲሆንልን ያደርጋል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር ለአንተ ሁሉንም ነገር ለመልካም ያደርግልሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon