ሁልጊዜ ተሞላ

ሁልጊዜ ተሞላ

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ መባከን ነውና፣ ኤፌ 5÷18 የእግዚአብሔር ቃል የሚያዝህ እለት እለት ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር መንፈስ እንድትሞላ እንደሆነ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ይህንንም ለማድረግ የመጀመሪያውን ሥፍራ ለእርሱ መስጠት በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ይ ደግሞ እራስን ሥርዓት ማስያዝ ይጠይቃል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ሌሎች ጉዳዮችም የእኛን ጊዜ ስለሚሻሙ ትኩታችንን ስለሚስቡ ነው፡፡ ሌሎች ብዙ ነገሮች የሚያስፈልጉንና የምንፈልጋቸው አሉ፡፡ ነገር ግን ምንም ነገር ከእግዚአብሔር የሚበልጥ የለም፡፡ በየቀኑ እግዚአብሔርን በቃሉ ውስጥ የመፈለግና ከእርሱ ጋር ጊዜ መውሰድ በጣም ቁልፍ የሆነ በመገኘቱ ውስጥ የመቆያ መንገድ ነው፡፡ የእራሱን ሃሣብ በጥንቃቄ ለመጠበቅ ሁልጊዜ በምሥጋና መንፈስ ውስጥ መቆየት በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ አንድ ጊዜ ወደ ሰው ሕይወት ከገባና ቦታ ከያዘ ለቆ አይሄድም፡፡ ለረጅም ጊዜያት ለቆ ላለመሄድ ይታገላል፡፡ ነገር ግን እኛም በበኩላችን እራሳችንን ከመንፈሳዊ ጉዳዮች ጋር አጥምደን መቆየት በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ማንኛውም ነገር በእሳት የሞቀ ቢሆንም እሳቱ እየጠፋ ሲሄድ ሙቀቱ እየቀነሰ እየቀዘቀዘ እንደሚሄድ ሁሉ መንፈሳዊ ጉዳይም እንዲሁ ነው፡፡

አንድ ወቅት እግዚአብሔር ለስድስት ወራት ምንም ዓይነት ሌላ ነገር በፊቱ በፀሎት ከእርሱ ማንነትና ከመራዳት ውጭ ወደ እርሱ እንዳልፀልይ በከለከለኝ ጊዜ ነበር፡፡ ወቅቱ በጣም ጥሩና ሥርዓትን የተማርኩበት ወደ እርሱም ለመጠጋትና የእርሱን ማንነት ለማወቅና በጥልቀት የበለጠ እንድቀርበው የረዳኝ ወቅት ነበር፡፡ በዚያ ወቅት ለመፀለይ ስቀርብ ‹‹እግዚአብሔር ይህ ጉዳይ ያስፈልገኛል›› ለማለት እነሳና እንደተከለከልኩ በማስታወስ ትቼ ‹‹ስለ አንተ እንዳውቅ እርዳኝ›› በማለት አስተካክል ነበር፡፡

እግዚአብሔር የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ይሰጠናል፡፡ እርሱ ሳንጠይቅም የሚያስፈልገንን ያውቃል፡፡ እኛ በእርሱ በመደሰት የእርሱ ረሃብ ውስጣችን ሲሞላ እርሱ ደግሞ የልባችንን ፍላጎት ይሰጡናል፡፡ እኔ ያማበረታትህ ለዛሬም ሆነ ለሁልጊዜ እራስህን በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ውስጥ እንድትጠብቅና ስለእግዚአብሔር ለማወቅ ከሁሉ ነገሮች በላይ ጥረት እንድታደርግ ነው፡፡ ስለሌላው ነገር ለቀረው ሁሉ እርሱ ይነቀቅልሃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔ ቃል ለአንተ፡- ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተህ ለመኖርህ እርግጠኛ ሁን

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon