ሂድበትና ታገኘዋለህ

ሂድበትና ታገኘዋለህ

ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛል፣ ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው፡፡ 1ቆሮ 16 9

አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔ ፈቃድ የማወቂያው ብቸኛው መንገድ መለማመድ ነው፡፡ እኔ በራሴ አባባል እንደምገልፀው ‹‹ሂድበትና ታገኘዋለህ ነው›› በሁኔታዎች ላይ ዝም ብዬ ብፀልይና ማድረግ ያለብኝን የማላውቅ ከሆነ ዝም ብዬ የእምነት እርምጃ እወስዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር እርሱን በታመነ መጠን ልክ በአውቶማቲክ በር ፊት እንደመቆም አድርጎ አሳየኝ በበሩ ፊት ቀኑን ሙሉ ቆመን ብንጠብቀው እኛ ወደፊት ተጠግተን የማሽኑን መክፈቻ እስካልነካን ድረስ አይከፈትም፡፡ በሕይወታችን አንዳንድ ወቅቶች የእራሳችን እርምጃ በመውሰድ ወደፊት የምንሄድበት ጊዜያት አሉ፡፡ በአንድም ሆነ በሌላ ማድረግ አለብን፡፡ አንዳንድ በሮች እኛ የእምነት እርምጃ እንደወሰድን የሚከፈቱ ወይም የሚሳኩ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የፈለግነውን ያህል ብንሞክር አይከፈትም፡፡ እግዚአብሔር በሮችን ሲከፍት ሂደበት፡፡ በሮችን ካልተከፈቱ ደግሞ በእግዚአብሔር በመርካት ሌላውን መንገድና እድል ተጠቀም፡፡ ነበር ግን በተስፋ መቁረጥ ከመሞከር አታቁም፡፡

በዛሬው ጥቅል ጳውሎስ በፊቱ የተከፈቱ ብዙ የበር እድሎች እንዳለና እንዲሁም በፊቱ ያሉትን ተቃዋሚዎች ይዘርዝራል፡፡ እኛም በእርግጠኝነት ማሳሳት ያለለብን ነገር ለተዘጉት በሮች ተቃውኖ እንደሌለ ማወቅ ነው፡፡

ጳውሎስና የእርሱ አብሮ ሰራተኞች የሆኑት ሲላሲና ባርናባስ የመለአክ መገለጥ ወይም የሠማይን ራዕይ የእግዚብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ቁጭ ብሎ ተቀምጦ አልጠበቁም፡፡ እርምጃ በመንገዳቸው ወስደው መቀጠላቸው ትክክል ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜ እግዚአብሄር መንገድ ይከፍትላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር መንገዶችን ይዘጋል፡፡ ይህ ደግሞ እነርሱን ተስፋ አላስቆረጠም፡፡ ነገር ግን በእምነት በመቀጠል እግዚአብሔር እንዲሰሩ የምፈልገውን በማግኘት ወደፊት ይሄዱ ነበር፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር በከፈተልህ በር በልበ ሙሉነት ሄደበት አንደኛውንም ስዘጋብህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon