ሃላፊነትን መውሰድ

ለሃጢአተኛ ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ አቤቱ አንተ የገሠፅኸው ህግህንም ህግህንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው፡፡መዝ 9412-133

ዎች ወይም ህይወት ስታሳዝነን፣ በእርጋታ ለመቀመጥና እግዚአብሔር ለህይወታችን ባለው ዓላማ መኖራችንን ለመቀጠል ሃላፊነት አለብን፡፡

መዝ 94፡12-13 ላይ እግዚአብሔር ያረጋጋናል እንደማይል ልብ ልንል ይገባናል፤ ክፍሉ ግን የሚለው ራሳችንን ለማረጋጋት የሚሆን ሃይል ይሰጠናል ነው፡፡ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር አጋሮች ነን፡፡ የእርሱ ድርሻ ችሎታን መስጠት ሲሆን፣ የእኛ ድርሻ ደግሞ ሃላፊነታችንን መወጣትና የተሰጠንን ችሎታ መለማመድ ነው፡፡

ሃላፊነት ስንል ‹ላለን ችሎታ ምላሽ መስጠት› ማለት ነው፡፡ ሃላፊነት የማይሰማው ሰው ስሜቱን ከመከተል ይልቅ ሁሉን ነገር እግዚአብሔር እንዲያደርግለት ይጠብቃል፡፡ ስሜታችሁ እንዲመራችሁ አትፍቀዱለት፡፡

እግዚአብሔር ስለ እናንተ ያስባል ፣ ግን የእናንተን ድርሻ አይወስድም፡፡ ጸንታችሁ ቁሙ ፣ ሀላፊነታችሁን ውሰዱ እና እርሱ ያቀዳትን የተባረከ ሕይወት እንዲኖራችሁ ከእግዚአብሔር ጋር መስራት ይጀምሩ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ፣ ቃልህ መረጋጋት የመቻል ችሎታ ሰጥተኸኛል ይላል ፡፡ ዛሬ እቀበላለሁ ፡፡ ስሜቶቼን ህይወቴን እንዲቆጣጠሩት አልፈቅድም ፣ እናም ሃላፊነቱን እወስዳለሁ ፤ አንተ የምትፈልገውን ምላሽም እሰጣለሁ ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon