በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን…. ኤፌ. 2÷5
ከእግዚአብሔር ጋር ኅብርት ማድረግ ሕይወታችንን ያገለግላል፡፡ ሕይወታችንን ያድሳል፡፡ የሕይወታችን ባትሪ እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ ያም ደግሞ እንድንናገር ያደርገናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረትና አንድነት ደግሞ ብርታት እናገኛለን፡፡ በዚህ ብርታት ደግሞ የነፍሳችንን ጠላት በመቋቋም መልሰን እናጠቃለን፡፡ (ኤፌ 6÷10-11 ተመልከት)
ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ሲኖረን ከጠላት የምንከለልበት የምስጥር ቦታ ውስጥ እንሆናለን፡፡ መዝ 91÷1 ይህ ጥቅስ የሚናገረው በዚህ ቦታ ውስጥ የሚኖር ጠላቱን ድል ያደርጋል፡፡ በልዕል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል ጥላ ውስጥ ያድራል፡፡ የእርሱን ኃይል የሚቋቋም ጠላት የለም፡፡
ይህ ምሥጥራዊ ቦታ የእግዚአብሔር መገኘት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ ስንሆን ከእርሱ ጋር ኅብረት ስናደርግ የእርሱን ሠላም እንለማመዳለን፡፡ ሰይጣን በቀላሉ የፈለገ ነገር ሲሆን በሁኔታዎች ውስጥ ፀንቶ በሚቆሙ አማኞች ሕይወት ላይ በቀላሉ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ለጊዜው እንዲህ ማድረግ ለጊዜው ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ በኩል ሕብረታችንን እያጠናከርን ስንሄድ ጥንካሬአችን እየበረታና እየተረጋጋን እንመጣለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ጥሩ ኅረት ለማድረግ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን የተወሰደው ጊዜ በመልካም ነገር ላይ የዋለ ነው፡፡ ብርታት ይሆነዋል እንጅ ዝም ብሎ ባላስፈላጊ ችግሮች ላይ የጠፋ ጊዜ አይደለም፡፡ ምሣሌ 18÷14 ላይ ‹‹የሰው ነፍስ ሕመሙን ያስታግሳል፡፡ የተቀጠቀጠን መንፈስ ግን ማን ያጠነክረዋል;›› ይላል፡፡ በችግር ውስጥ እስክትጠነክር አትጠብቅ ጠንክረህ ቁም፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ሁኔታና ችግር ውስጥ እያለፍክ ብሆን አይገድህም በክርስቶስ በኩል ድል አለህ፡፡