ህብረት በረከትን ያመጣል

ህብረት በረከትን ያመጣል

ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና። (መዝ 133፡ 1-3)

ብቻህን ስለአንድ ነገር በምትፀልይበት ጊዜና ፀሎትህ ያልተሰማ ሲመስልህ፤ ካንተ ጋር በህብረት ተስማምቶ ሊፀልይ የሚችል ሰዉ ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡ እነደዚህ አይነት ህብረት ጉልበት ያለዉ ሀይልን የሚያመጣ መንፈሳዊ ለዉጥ ነዉ፡፡ እንደዛሬዉ ቃልም መልካም የሆነ ነገርና የእግዚአብሔርን በረከት እንዲመጣ የሚያደርግ ነዉ፡፡

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ያሉ ሰዎች ሲስማሙ ጌታ ኢየሱስ ከእነሱ ጋር ለመሆን ቃል ይገባል፤ የሱ መገኘት ደግሞ በህይወታችንና በሁኔታዎቻችን ላይ ከምንገምተዉ በላይ ኃይል እንዲኖር ያደረጋል፡፡ በማቴዎስ 18፡ 19-20 ሲናገር፤ “ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”

እግዚአብሔር ለብቻችንም ስንሆን ከኛጋር ይሆናል፤ በህበረትና ስምምነት አንድ ላይ ስንሆን ደግሞ ጉልበታችን ይጨምራል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገርም ፤ አንድሰውእንዴትሺህንያሳድድነበር?
ሁለቱሳእንዴትአሥሩንሺህያሸሹነበር? ይላል (ዘዳግም 32:30 ን ተመልከቱ) ፡፡ እኔ እነደዚህ ያለዉን ስሌት እወዳለሁ፡፡

ምክንያቱም የእገዚአብሔር በረከት በህብረት ላይ፤ ህልዉናዉ ደግም በስሙ ከሚሰማሙት ጋር ነዉ፡፡ ጠላት ህብረትን በማበላሸት ሰዎች እርስ በእርስ እንዲቃረኑና እነዲከፋፈሉ ለማድረግ ተግቶ ይሰራል፡፡ የህብረትን ኃይል/ጉልበት መረዳት እነዲሁም የእግዚአብሄርን ድምጽ ከሌሎች ጋር አብረን ሆነን መስማትን መለማመድ ይገባናል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ከሌሎች ጋር እብሮ በህብረት መፀለይን አትተዉ፡፡”

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon