‹‹ … ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ›› (ዮሐ.19፡30) ።
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ውሎ ‹‹ተፈጽሟል›› ብሎ ሲናገር ይህም ማለቱ የኃይማኖታዊ ህጋዊ ሥርዓት ተፈጽሟል ማለቱ ነው፡፡ ያም አሁን የኃይማኖታዊ ሊቀካህን ብቻ ወደ እግዚአብሔር መገኘት መግባት ይችላል ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሁሉም ህዝቦች በህልውናው መደሰት ለእርሱ መናገርና ድምጹን መስማት ይችላሉ ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ከመሞቱ በፊት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የመቀበያ ብቸኛው መንገድ ፍጹም ህይወት፣ ኃጢአት የሌለበት (እጅግ ህግ ጠባቂ መሆን) ወይም ለኃጢአት ከታረዱ እንስሳት መስዋዕት ማቅረብ ነበር፡፡ ኢየሱስ ሞቶ የኃጢአት እዳ በደሙ ለሰው ልጆች ሁሉ በከፈለ ጊዜ እርሱ ሁሉም ሰው በግሉ ወደ እግዚአብሔር ህልውና በመቅረብ እንዲደሰት በር ከፈተ፡፡ ኢየሱስ ‹‹ተፈጸመ›› ባለ ጊዜ እርሱ ሁላችንም ከፍርሃት ይልቅ ወደ አርነት ህይወት ጋበዘን (ጠራን)፡፡ ይህም ህይወት በህግና በመመሪያ ከመመራት ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ ለመመራት ወደሚያስችል ህይወት ጠራን፡፡ ማንኛውም ተራ ሰው ሁልጊዜ ሁሉንም መልካም ነገር ለማድረግ የማይችለው ሰው አሁን ወደ እግዚአብሔር ህልውና በነጻ መግባትን ቻለ፡፡
ከህጋዊነት አርነት መውጣት ማለት ለስንፍናና ለዓመጸኝነት መጠራት ማለት አይደለም፡፡ እያንዳንዳችን የእግዚአብሔርን ቃል መማርና የራሳችን ከእግዚአብሔር የመስማት ኃላፊነታችን ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ከእኛ ሁልጊዜ የሚፈልገው ነው፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር ይወዳሃለህ እንዲሁም ባለህ ህይወት ደስተኛ እንድትሆን ይፈልጋል፡፡