
እግዚአብሔርም ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም፡፡ዛሬ የምሰጥህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቅ መቼውንም ቢሆን እላይ እንጂ ፈጽሞ እታች አትሆንም፡፡ – ዘዳ 28፡13
በህይወቴ ጥቂት ታላላቅ ድሎችን አግኝቼያለሁ፡፡እግዚአብሔር ከእጅግ ብዙ የድሮ ሀጢያቶቼ፣እስራቶቼ እና ልማዶቼ ነጻ አውጥቶኛል፡፡ የተለማመድኩት ሰላም ጥልቀት እጅግ አስደናቂና እግዚአብሔር ሁላችንም እንድንለማመደው የሚፈልገው ነው፡፡
አሁንም ላሸንፋቸው የሚገቡኝ ጦርነቶች እና ላልፋቸው የሚገቡ እንቅፋቶች አሉብኝ እናንተም እንዳለባችሁ እርገጠኛ ነኝ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ለማስተካከል ልትሰሩበት የምትፈልጉትን አንድ ነገር እንድትመርጡ አበረታታችኋለሁ፡፡
ቀጥሎ ደግሞ ዛሬ በክርስቶስ ልታገኙት የምትችሉትን ድል እየኖራችሁ ራሳችሁን እዩት፡፡ነጻ ስትሆኑ ህይወታችሁ ምን እንደሚመስል አስቡ፡፡
ዘዳግም 28፡13ን የተጠቀምኩበት እንደ ማበረታቻ ነው፡፡ሙሉውን ምዕራፍ እንድታነቡት አበረታታችኋለሁ፡፡የሚናገረው መሰረታዊ ነገር እግዚአብሔርን ከታዘዛችሁ ይባርካችኋል እግዚአብሔርን ካልታዘዛችሁ የተረገማችሁ ትሆናላችሁ ነው፡፡ይሄ ሀይለኛ ማበረታቻ ነው፣አትስማሙም?
ነገሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና በጠላት ላለመመራት ከእግዚአብሔር ጋር መስራትን እወዳለሁ፡፡ እንደውም “እግዚአብሔር ሆይ ለመለወጥ እፈልጋለሁ፡፡አንተን ማስደሰት እፈልጋለሁ፡፡” ማለት በህይወት አስደሳቹ ጉዞ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ወደ እንደዛ አይነት የአስተሳሰብ ክልል ስትገቡ ከአንድ ነገር ነጻ ወጥታችሁ ወደሌላ ከዛም ወደሌላ እናም በቅርብ ጊዜ ውስጥ በክርስቶስ ባላችሁ ስልጣን እየተራመዳችሁ እንደሆነ ትረዱታላችሁ፡፡
ህይወታችሁን ደስ በሚል መንገድ ከማደግ እና ከመቀየር ውጪ አትኑሩት አለበለዚያ እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ ሊሰራቸው የሚችላቸው መልካም ነገሮች ያመልጣችኋል፡፡
ወደፊት መሆን የምትፈልጉትን ሰው ዛሬ ጊዜ ወስዳችሁ አልሙትና የእግዚአብሔርን ነጻነት መከታተል ጀምሩ፡፡ምክንያቱም አንድ ቀን ላይ በማተኮር እናንተ እና እግዚአብሔር ምንም ማድረግ ትችላላችሁ!
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ነጻነትህን መለማመድ እችላለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ዛሬ ራሴን ባንተ ነጻነቱን እንዳገኘ ሰው እቆጥራለሁ፡፡ስኖር አንተን እንዳስደስት እና አንተ በሰጠኸኝ ስልጣን እንድመላለስ ሀይልህን ስጠኝ፡፡