ለሌሎች መጸለይ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ

ለሌሎች መጸለይ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ

የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። – ሉቃ 6፡28

አንድ ሰው ስሜትህን ሲጎዳው እንዴት ነው የምትመልስለት? ደስታህን እንዲወስድብህ ትፈቅድለታለህ? ወይስ ስሜትህን እንደፈለገ እንዲሆን ትለቀዋለህ?

ሉቃ 6፡28 ሰዎች ሲጎዱን ማድረግ ያለብንን በተመለከተ ልንጸልይላቸውና ልንባርካቸው ይገባል በማለት ይነግረናል፡፡ የሚረግሙን ሰዎች ደስተኞች እንዲሆኑ መጸለይ ተፈጥሯዊ ምላሽ አይደለም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጥበብ ከእኛ ጥበብ ከፍ ያለ ነው፡፡ ምንም እንኳ ጥሩ ስሜት ባይሰማንም ማድረግ ያለብን ትክክለኛው ነገር ይሄው ነው፡፡  እንዲ ብላችሁ ጸልዩ ጌታሆይ እኔ በመታዘዝ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ፡፡ ጌታ ሆይ የጎዱኝን ሰዎች መባረክ እንደ በረከት አይሰማኝም ነገር ግን አንተ እንደፈለግህ እንድታደርግ እጸልያለሁ፡፡ ምክንያቱም አንተ የነገርከኝ በመገኘትህ እንዲባረኩ ነው፡፡

እግዚአብሔር እንድናደርገው ከጠየቀን ነገሮች መካከል በጣም ከባዱ ነገር ለጎዱን ሰዎች እንድንጸልይ የጠየቀን ጥያቄ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የጎዱን ሰዎች በጣም ስህተትና ይቅርታ አይገባቸውም ብለን የምናስብ ከሆነ ደግሞ በጣም ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን ይቅርታን እንድንለማመድ እግዚአብሔር አዞናል፡፡ የይቅርታን ጎዳና ለመከተል በምንመርጥበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ከመታዘዝ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ሰላምና ደስታ እንለማመዳለን፡፡ እግዚአብሔርን ስትታዘዝ የመሰናክልን ህመም ማሸነፍ እንድትችልና በሕይወት የበለጠ እንድትደሰት ይረዳናል።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ከባድ ቢሆንም እንኳን ለጎዱኝ ሰዎች እጸልያለሁ፡፡ የአንተ በረከትም እንዲሆንላቸው እጸልያለሁ፡፡ ጉዳቴን ከልቤ በማውጣት ይቅር እንድል እርዳኝ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon