ለሌሎች አድርጉላቸዉ

ለሌሎች አድርጉላቸዉ

እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና። – ማቴ 7፡12

እግዚአብዘሔር በህይወታችን ሊያፈሳቸዉ የሚፈልገዉ ብዙ በረከት አለዉ፤ እጅግ ብዙ በረከት ነገር ግን እኛ እንዲደረግልን የምንፈልገዉን ነገር ለሌሎች ማድረግ ስላልቻልን ብቻ የማናዉቃቸዉ ብዙ በረከቶች አሉ፡፡ እኛ በሌሎች መባረክ እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ያለ ራስ ወዳድነት በቅድሚያ ሌሎችን ለመባረክ እንወዳለንን?

ጋብቻህ፣ ቤተሰብህና ጓደኝነትህ እንዲሆኑ የምትፈልገዉን ካልሆኑ፤ ይህንን መርህ በመጠቀም እነርሱን መቀየር ትችላለህ፡፡

ምንአልባት ባለቤትህ አንድ ነገር እንድታደርግልህ እየጠበቅህ ይሆናል ወይም ምንአልባት ጓደኞችህ ቀድመዉ እንዲረዱህ ስለፈለግህ እነርሱን መርዳት አልፈለግህ ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ መኖር በራስ ወዳድነት ምቹ ሊያደርግህ ይችላል፡፡ ነገሮችን ለመለወጥ አንተ እስካልወሰንክ ድረስ ነገሮች አይለወጡም፡፡ ራስህን ትሁት ልታደርግና ግንኙነቶችህን ልታድን ጊዜዉ አሁን ነዉ፡፡

በረከት ወደ መንገድህ እንዲመጣ በመጠባበቅ ፈንታ እግዚአብሔር በህይወትህ ያመጣቸዉን ሰዎች በመስዋዕትነት ለማገልገል ምርጫ አድርግ፡፡ አገልጋይ ሁን ሌሎችን መባረክ ትኩረትህ አድርግ፡፡

ተቀባይነት ያጣህና የተወገዝክ አድርገህ በማሰብ ፈንታ፤ ሌሎች አንተን እንዲያደርጉልህ በምትፈልገዉ መንገድ ሌሎችን ስትንከባከብ ግንኙነትህ እንዴት እንደሚያድግ በማየት ትደነቃለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ራስ ወዳድ ህይወት በመኖር የማገኘዉ ምንም የለም፡፡ ሰዎች ለእኔ መልካም እንዲሆኑ በመጠበቅ ፈንታ ለእነርሱ ቅድሚያ መልካም መሆን አለብኝ፤ እኔን እንዲይዙኝ በምፈልገዉ መንገድ ሌሎችን መያዝ እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon