ለሕይወትህ ኃይል ያስፈልጋል

ለሕይወትህ ኃይል ያስፈልጋል

እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፣ እኔም ይህን ብቻ ሰማው፣ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፡፡ መዝ 62÷11

ፀሎት፡- በቀላሉ ለእግዚአብሔር መናገርና እግዚአብሔርን እንድናገርና ማዳመጥ ሲሆን ካሉት ኃይላት ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው በዓለማት ካሉ ሁሉ በላይ ኃይል ያለው እንዳረገ አምናለሁ፡፡ ይህ ጠንከር ያለ ንግግር አሁን ካሉት ኃይላት በላይ የሆነና ምንም ጥርጣሬ የሌለው እውነት ነው፡፡ ስለ ኒውክለር ኃይል ወይም አውቶሚክ ኃይል ካሉት ሁሉ በላይ የበለጠ ኃይል እንዳላቸው እናስባለን፡፡ እንዲሁም መኪና እና ሞተር ሳይክልም የየራሳቸው ኃይል አላቸው፡፡

ነገር ግን የምድር ታላቅ ኃይል ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር አይወዳደርም፡፡ እኛ የምናውቀው ውጫዊ ኃይላት ተፈጥሮአዊ ናቸው፡፡ ነገር ግን የፀሎት ኃይል መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡ ፀሎት የእግዚአብሔርን ኃይል በዕለት ሕይወታችን የሚያስለቅቅና የፀሎት ኃይል እኛን ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር ያጣብቀናል፡፡ ለዚህም ነው ፀሎት ከማንኛውም ጉልበት ሁሉ በላይ ነው የምንለው፡፡

የፀሎት ኃይል የእግዚአብሔርን እጅ እንድናንቀሳቅስ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር የግለሰቦችን ልብ መለወጥ ይችላል፡፡ ግለሰቦችን ከሱስ እስር ነፃ ያወጣል ከሚያስጨንቅ አስደንጋጭ ነገር ይፈታል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነውን ይፈታል ይገለብጣል፡፡ የሰዎችን ስሜት ይፈውሳል፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል ጋብቻን ያድሳል፡፡ የውጤታማነትንና የዕቅድን ፀጋ ያካፍላል፡፡ ሠላምና የልብ ደስታ ያመጣል፡፡ ጥበብን ይሰጣል፡፡ ተዓምር ያደርጋል፡፡ የሚያስፈራ ነገር ያደርጋል እጅግ በጣም ብዙ የእግዚአብሔር ኃይል በዓለም ውስጥ ያለውን የሚለቀቀው ቀላል በሆነ የእምነት ፀሎት ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በፀሎትህ የእግዚአብሔር ኃይል በሕይወትህ እንዲለቀቅ አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon