ለመለወጥ መፍቀድ

ለመለወጥ መፍቀድ

ሕይወትን እና ሞትን፣በረከትና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ፡፡እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፡፡ – ዘዳ 30፡19

ጨስ የጀመርኩት የዘጠኝ አመት ልጅ ሆኜ ነበር፡፡ስለሚያዝናናኝ እወደው ነበር እናም ለረጅም ጊዜ ማቋረጥ አልፈለግኩም ነበር፡፡ማቋረጥ እንዳለብኝ ባወቅኩበት ሰአት ማቋረጥ አልፈለግኩም ምክንያቱም ያወፍረኛል ብዬ አስቤ ስለነበር ነው፡፡ለአመታት የማምለጫ ምክንያቴ ይሄ ነበር፡፡ከዛ ደግሞ እያቆምኩ እንደገና የመጀመር አዙሪት ውስጥ ህይወቴ ገባ፡፡

ከፍተኛው የቀውስ ደረጃ ላይ የደረስኩት ግን በጣም ማጨስ ሲያስፈልገኝ ከቤተ-ክርስቲያን አቋርጬ እየወጣሁ መኪናዬ ወንበር ላይ ተኝቼ ማጨስ ስጀምር ነው፡፡ይሄኔ ነበር መለወጥ እንዳለብኝ የገባኝ፡፡

ብዙ ጊዜ ብዙዎቻችን ለመለወጥ ከመፍቀዳችን በፊት የሆነ ቀውስ ይመጣል፡፡ለምሳሌ አንዳንድ ሰው በልብ ድካም መያዙን ሲያውቅ ትክክለኛ ምግም መመገብ ይጀምራል፡፡ነገር ግን የሆነ ቀውስ እስኪያጋጥማችሁ መጠበቅ የለባችሁም፡፡ቆርጣችሁ በመነሳት “በቃኝ ከዚህ ነገር ጋር አልቀጥልም” ማለት አለባችሁ፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ህይወትን መምረጥ ትችላላችሁ ይላል፡፡እግዚአብሔር ለመለወጥ ዕርዳታውን እና ችሎታውን ሰጥቷችኋል ነገር ግን ፈቃደኛ መሆን አለባችሁ አለዛ ቀውስ ድንገት እና ፈጣን በሆነ መንገድ ያጋጥማችኋል፡፡ወደ እዛ ነጥብ ከመድረሳችሁበ በፊት ህይወትን መምረጥ በጣም ቀላል ነው፡፡

ለተወሰነ ጊዜ ምቾት ማጣትን አትፍሩ፡፡በመጨረሻ ከማጨስ ነጻ ወጣሁ እናም ቀላል አልነበረም…ነገር ግን ብቻዬን ማድረግ አልነበረብኝም፡፡

ለመለወጥ ዝግጁ ነኝ ብላችሁ ካላመናችሁ ወደ እግዚአብሔር ሂዱ እና “እርዳኝ፣እርዳኝ፣እርዳኝ” በሉት፡፡

መልካሙ ዜና ህይወትን ለመምረጥ በእግዚአብሔር ዕርዳታ እና በእናንተ በኩል በተደረሰ ውሳኔ ዘላቂ በሆነ መንገድ ለተሻለ ነገር መለወጥ ትችላላችሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ምርጫን ሰጥተኸኛል እናም ህይወትን መርጫለሁ! ለውጥ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡እንድትረዳኝ እጠይቅሀለሁ፡፡በአንተ ዕርዳታ እና በእኔ ለመለወጥ ፈቃደኛ መሆን ማንኛውንም ዕንቅፋት እንደማሸንፍ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon