ለምታምናቸዉ ሰዎች ድክመትህን ተናዘዝ

ለምታምናቸዉ ሰዎች ድክመትህን ተናዘዝ

የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። – ሉቃ 8፡17

ብዙ ሰዎች ስለ ስህተታቸዉና ስለ ድክመታቸዉ ማዉራት ምቾት አይሰጣቸዉም፡፡ ለምድነዉ ነገሮችን ወደ ግልጽነት ማምጣት የማንወደዉ? ምክንያቱም ሰዎች ሊያስቡት ስለሚችሉት ነገር ስለምንፈራ ነዉ፡፡ የምንፈራዉ በሰዎች እንጠላለን፣ ሰዎች በስህተት ይረዱን ይሆናል፣ አይወዱን ይሆናል፣ ስለ እኛ ሁሉን ሲያዉቁ አመለካከታቸዉ ይቀየር ይሆናል ስለምንል ነዉ፡፡

ነገር ግን ስህተታችንን መናዘዝ ስሜታዊ ፈዉስ ያመጣልናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም የተሰዎሩ ነገሮች ወደ ግልጽነት እንደሚመጡ ይናገራል ስለዚህ ዛሬ ለምናምናቸዉ ሰዎች ጉዳታችንንና ድካማችንን ማካፈል አለብን፡፡

በመጨረሻም በሕይወቴ ስላለፈዉ በደልና ብዝበዛ ለመናገር መደፋፈር የጀመርኩ ጊዜ ለስሜቴ ከባድ ነበር፣ ነገር ግን አሁን ስናገረዉ ልክ ስለሌላ ሰዉ የምናገር ያህል ይቀለኛል፡፡ በህይቴ ያለዉን ህመምና ድካም የመናዘዝ ሂደት ለሕይወቴ ፈዉስና ታሃድሶ አምጥቶልኛል፡፡

ድካምህን ለመናዘዝና ግልፅ ለመሆን ልታምናቸዉ የምትችላቸዉን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲያሳይህ ጸልይና ተግብረዉ፡፡ እርስ በእርስ መናዘዝ ስትጀምሩ አንዳችሁ ለአንዳችሁ የእግዚአብሔርን ፈዉስ ታመጣላችሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ስህተቴን፣ ድካሜንና ህመሜን እንዳካፍል በህይወቴ ያስቀመጥከዉ ሰዉ ማን እንደሆነ አሳየን፡፡ በእኔም በእነርሱም ህይወት ለሚመጣዉ ታላቅ ፈዉስ በሮቼን እከፍታለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon