ለሠላሙ ተጠባበቅ

ለሠላሙ ተጠባበቅ

እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፣ ሠላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና፡፡ መዝ 85÷8

እግዚአብሔር ስናገረን የሰማነው መልዕክት በእርግጥ ከእርሱ የሰማን መሆኑን ለማረጋገጥ ጥልቅ የሆነ የልብ ሰላም እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ የእውነት መንፈስ የመረጋጋት የውስጥ የነፍስ ፀጥታ እንዲሰማን ያደርጋል፡፡

ሸንጋይ የሆነ ጠላታችን ሲነገረን በሰላም አይሰማንም፡፡ በራሳችን መንገድ ችግሮችን መፍታት ስንሞክር ሠላም አናገኝም ምክንያቱም ሥጋዊ አእምሮ ከመንፈስ ቅዱስ ውጭ የሆነው በስሜትና በሰበብ ላይ ብቻ የተመሠረተው የሞቱና ነገሮች ሁሉ ከሃጥያተኛ ማንነት አንፃር የሚያመዛዝንና የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ በአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ዘላቂ መፍትሔ አይሠጥም፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ የሆነ አእምሮ ግን ሕይወትና ሠላም ነው ለአሁኑም ሆነ ለሁሉም፡፡ ሮሜ 8÷6

መቼም ቢሆን የሚታምነው እግዚአብሔር ሲናገር ወይም ውሳኔም የምታደርገው እሱ ያለውን ስታምን የሠላምህና ሚዛን በመጠበቅ መሆን አለበት፡፡ ሠላም የተቀበልከውና የሰማውን መመሪያ ሚዛን ካልጠበቀ ልትቀጥልበት አይገባህም፡፡ ለሌሎች በጉዳዩ ላይ ለምን ሠላም እንዳጣ ማስረዳት አይጠበቅብህም፡፡ አንተም እንኳ ለራስህ ላታውቅ ትችላለህ፡፡ አንተ በቀላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ለእኔ ሠላም የተሰማኝ አይደለም›› ስለዚህ አሁን በዚህ ነገር (ጉዳይ) መቀጠል አልችልም በማለት እርምጃ መውሰድ ጥበብ ነው፡፡

ሁልጊዜ ለሰበከው ወይም ላቀድከው ጉዳይ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ግልፅ እስከሆነልህና ነፍስህን ሞልቶ ሙሉ ሠላም እስኪሰጥህ ድረስ መጠበቅ አለብህ፡፡ ሠላም ትክክለኛ ከእግዚአብሔር ለመስማትና ትክክለኛ ጊዜ እርምጃ የምትወስድበት ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡ ሠላም ድፍረትና እምነት እግዚአብሔርን የሚሰጠንን ትዕዛዝ ለመታዘዝ የሚያስችለን ማረጋገጫ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ሠላም እስኪሠማና እስክታረጋግጥ ድረስ እርምጃ አትውሰድ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon