ለራስህ አትዘን

ለራስህ አትዘን

ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም። – ኤርሚያስ 29፡11

ራስን አሳዛኝ አድርጎ መቁጠር አሉታዊ እና አፍራሽ ስሜት ነው፡፡ ከፊት ለፊታችን የሚጠብቁን እድሎች እና በረከታችንን እንዳናይ ያሳውረናል ለዛሬ እና ለነገ ያለንንም ተስፋ ይሰርቅብናል፡፡ ራሳቸውን አሳንሰው የሚያዩ ሰዎች ሲጀምር ለምን አንዳች ነገር ለማድግ እሞክራለሁ? መጨረሻዬ እንደሆነ መውደቅ ነው ብለው ያስባሉ፡፡

ራስን አሳንሶ ማየት በእርግጥም ወደ ሌላ ጥግ ትኩረት ያደረገ በራስ ላይ ትኩረት ያደረገ የጣኦት አምልኮ ነው፡፡ ራሳችንን አሳንሰን በማየት ውስጥ የእግዚአብሔር መሰረታዊ ፍቅር ከመግፋቱም በላይ ነገሮችን ሊለውጥ ይችላል የሚል እምነትን ይክዳል፡፡

ራሳችሁን አሳንሳችሁ በማየት የምታሳልፉበት አንድም ቀን እንዳይኖር አበረታታችኋለሁ፡፡ ተስፋ ስታጡ እና ለራሳችሁ ስታዝኑ ቆም ብላችሁ ‹‹ ለራሴ ማዘንን እቃወማለሁ ፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብሆንም የተሸሉ ነገሮችን ተስፋ አደርጋለሁ›› ብለችሁ ተናገሩ፡፡

ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም። እምነታችሁን በኢየሱስ ላይ ካደረጋችሁና ትኩረታችሁን ተስፋ በምታደርጉበት ላይ ካደረጋችሁ አስደናቂ ነገር በሕይወታችሁ ውስጥ ይከሰታል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ለራሴ ማዘንን እቃወማለሁ፡፡ ሁኔታዎች አስቻጋሪ ሲሆኑ አንተ ከችግሬ በላይ ታላቅ እንደሆን አስባለሁ፡፡ አንተ ለኔ መልካም እቅድ አለህ፡፡ እቅድህ በሕይወቴ ይፈጸም ፡፡ በአንተ እታመናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon