ለሰዎች ቅድሚያ ስጥ

ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አስተምራችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መፀለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ፡፡ 1 ሣሙ. 12 23

ለውጤታማ ፀሎት አንዱ ቁልፍ ነገር ለሌሎች ሰዎች ትኩረት በመስጠት እንጂ በራስ ፍላጎት ላይ ብቻ በማተኮር አይደለም፡፡ በራሳችን ጉዳይ ላይ በእግዚእሔር ፊት ልንፀልና ልንጠይቅ በእውነት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ ለእራሳችን ብቻ መፀለይን በማስተካከል ሌሎችም መፀለይ ብዙውን ጊዜ ውጤታማ አይደለም፡፡ ስለዚሀ ፀሎታችንን በመገምገምና ለሌሎች እየፀለይን እንደሆነና እንዳልሆን ለይተን ለሌሎችም ለመፀለይ ጊዜ ሊኖረን ይገባል፡፡ የአራትና የአምስት ሰዎችን የፀሎት አርዕስት በተከታታይ ሳደምጥ እንድፀልይላቸው ያቀረቡትን የብዙዎቻቸው ፀሎት መልስ ወዲያው መልስ ሲመጣ ሌሎች ደግሞ ለእርስ በርስ እንዲፀልዩ እንዳደርጋቸው መረዳት መጣልኝ፡፡ ምናልባትም የአንዱ ከሌላው ሕይወት ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡ የአንዳንዱ ምናልባት በቅርብ የምወደውን በሞት ያጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዱ የሥራ በር እንዲከፈትለት የምፈልግ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዱ የሚኖርበትን ቦታ የሚፈልግ ይሆናል፡፡ አንዳንዱ ስለጤናው ጥሩ ያልሆነ መረጃ ከሐኪሙ የሰማ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዱ ደግሞ ልጅ ታሞበት ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው ደግሞ ከባለቤቱ ጋር የተለያዩ ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች የተለያየ ፍላጎት ወይም ጥያቄ አላቸው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ደግሞ የእኛ ፀሎት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እግዚአብሔር እኛ ለእርስ በርሳችን በታማኝነት በፍቅርና በርህራሄ እንድንፀልይ ይፈልጋል፡፡ እኛ ለሌሎች በምንፀልይበት ወቅት መልካ ዘር በሕይወታችን ጥሩ ፍሬ የሚያመጣውን እየዛራን ነን፡፡

እኔ በማገለግልበት ኮንፍራንስ ተገኝታ ፕሮግራሙን የተካፈለችውን ሴት ምስክርነት አስታውሳለሁ፡፡ በዚያ ፕሮግራም ላይ ሰዎች ከበሽታቸው እንዲፈውሱ ዝም ብላ ለእርሷ እንኳ መፀለይ እስክትረሳ መፀለይ ቀጠለች፡፡ ለእራሷ ምንም እንኳ የደም ካንሰር በሽታ ቢኖርባትም ለሌሎች ሰዎች ትፀልይ ነበር፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ከሒክማ ጋር የምርመራ ቀጠሮ ስለነበረባት ስትሄድ ምርመራ ካደረጉላት በኋላ ምን እንደሆነ ባናውቅና ነገሩ ባይገባንም በሽታው በደምሽ ውስጥ የለም አሏት፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ሌሎችን ለመርዳት በተዘረጋህ መጠን እግዚአብሔር አንተንም ሊረዳህ ይዘረጋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon