ለስላሳና ስሜት (ደንታ ያለው)

ለስላሳና ስሜት (ደንታ ያለው)

ለእግዚአብሔር ድምፅ ለስላሳና ትህትና ያለው ልብ ይኑርህ በትዕዛዜም ይሄዱ ዘንድ ፍርዴንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፡፡ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ እሰጣለሁ፡፡ ከሥጋቸውም ውስጥ የድንጋዩን ልብ አወጣለሁ፡፡ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ፡፡ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፡፡ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፡፡ ሕዝ 11÷19

በዛሬው ቀን ጥቅሳችን እግዚአብሔር የድንጋይ ልብን ወደ ስጋ ልብ እንደሚለውጥ የተስፋ ቃል የገባበት ነው፡፡ በሌላ ቃል እርሱ ጠንካራውን ልብ ወደ ለስላሳና ትሁት ልብ መለወጥ ይችላል፡፡ ለእግዚአብሔር ሕይወታችንን አሳልፈን ስንሰጥ እርሱ በሕሊናችን ውስጥ እውነትና ሃሰትን የመለየት ስሜት በውስጣችን ይኖራል፡፡ ግን ለብዙ ጊዜያት ደጋግመን ሕሊናችን ከተቃወምን ወይም ከተቃረን እኛ ተመልሰን ልባችንን የጠነከረና እየደነደነ ይመጣል፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ከተከሰተ እግዚአብሔር ልባችንን ሊያለሰልስ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ለመንፈሳዊ ጉዳይ ኖሮን ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስሜት ይኖረናል፡፡

እኔ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብርት በደንብ ማድረግ ሳልጀምር ልበ ደንዳና ነበርኩ በየጊዜው በተከታታይ ከእርሱ ጋር በኅርት በማሳለፍ ልበ ልልና በድምፅ በጣም ስሜታዊ እየሆንኩ መጣሁ፡፡ ለእግዚአብሔር ስሜታዊ ሳንሆን የእግዚአብሔርን መንካት ስለማንገነዘብ ብዙውን ጊዜ እኛ ሲነገረን ድምፁን ሳናስተውል እናልፋለን፡፡ እርሱ በእርጋታ ይናገረናል፡፡ በቀስታ በትንሽ ድምፅ ስለነገሮች በትህትናና በፀና እምነት ይነገረናል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ልበ ደንዳና ሰዎች ለራሳቸው በአደጋ ሥር መሆናቸው ብቻ ሣይሆን ሌሎችን መጉዳት ምክንያት መሆናቸውን እንኳ አያውቁም፡፡ ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ያሳዝናል፡፡ እነዚያ ልበ ደንዳኖችና የራሣቸውን ሥራ በመስራት የተጠመዱት ለእግዚአብሔር ፈቃድና ድምፅ ደንታ (ስሜት) የላቸውም፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ ልባችንን በቃሉ ሊያለሰልስ ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ልበደንዳኖች የእርሱን ድምፅ መስማትም ሆነ ብዙ በርካቶች እርሱ ሚዘረጋላቸውን ለመቀበል አይችሉም፡፡


ዛሬ የእግዚአአብሔር ቃል ለአንተ፡- ልብህን ለእግዚአብሔር ድምፅ ለስላሳና ስሜት (ደንታያለው) አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon