ለስላሳውን የዝምታ ድምጽ መስማት

ለስላሳውን የዝምታ ድምጽ መስማት

ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። – 1 ነገ 19፡12

በህይወትህ ውስጥ ሰላምን ለማግኘት በየቀኑ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ወስጣዊ መነሳሳት መታዘዝ አለብህ፡፡ መነሳሳት ማለት እግዚአብሔር በውስጥህ እንድታደርገው የሚነግርህ ነገር ማለት ነው፡፡ 1ነገ 19፡12 እንደተገለጸው የዝምታ ድምጽ ማለት ይህንን ነው፡፡ ተነሳሽነት በመዶሻ አናት ላይ እንዳለ መምቻ አይደለም፡፡

በ1ነገስት ላይ እንደምናበው እግዚአብሔር ኤልያስን ለማነሳሳት ትልቅና ጠንካራ ነፋስ ወይም ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጥና እሳትን አልነበረም የተጠቀመው፡፡የእግዚአብሔር ድምጽ ለስለስ ባለ የጸጥታ ድምጽ ነበር ወደ ኤልያስ የመጣው፡፡ ይሄ ምናልባትም ድምጽ ላይሆን ሁሉ ይችላል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከጆሮ ይልቅ ለልብ በመናገር ምሪትን ሊሰጥ ይችላል፡፡

እግዚአብሔርን ብናዳምጥ እና የተናገረውን ሁሉ ብናደርግ ሁሉም ነገሮች መልካም እንደሚሆንልን እናውቃለን፡፡ ሁኔታዎች ምንም ይሁኑ ምን እግዚአብሔርን መስማትና ድምጹን መታዘዝ አለብን፡፡ እግዚአብሔር አንድ ነገር እንድታደርጉ ሲጠይቃችሁ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ላትረዱት ትችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድምጹን ስትሰሙና የሰጣችሁን ምሪት ስትታዘዙ በእርሱ ሰላም ውስጥ ታርፋላችሁ፡፡ ስለዚህ አድምጡት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ፤ አንተ በየዕለቱ በልቤ ውስጥ የምታመጣውን ድምጽ ማዳመጥ እንድችል እርዳኝ፡፡ የአንተን ሰላም እፈልጋለሁ፡፡ ስለዚህ እሰማሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon