ለተራራዉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገር

ለተራራዉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገር

እዉነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህንን ታራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባህር ተወርወር’ ቢለና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢለምን ይሆንለታል፡፡ – ማር 11:23

ኢየሱስ ለተራሮች እንድንናገርና ወደ ባህር ተነስተው  እንዲወረወሩ እንድናዝ ሲናገር ታላቅ መግለጫ እያደረገ ነበር፡፡

አያችሁእኛ ዘወትር የምንናገረዉ ስለ “ተራሮች” ወይም ስለ ተግዳሮቶቻችን ነዉ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚያዘን እንድናናግራቸዉ ነዉ፡፡ ይህንን ስናደርግ የግድ ለነሱ መመለስ ያለብን ከእግዚአብሔር ቃል ነዉ፡፡

በሉቃስ 4 ሳይጣን ኢየሱስን በምድረ በዳ ሊፈትነዉ ሲሞክር፤ ለእያንዳንዱ ፈተና ጌታ የመለሰለት ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ነዉ፡፡ በተደጋጋሚ ይጠቅስ የነበረዉ የዲያብሎስን ሐሰትና ሽንገላ የሚያፈርሱ ጥቅሶችን ነበር፡፡

እኛ እንደዚህ ዓይነት ነገር የመሞከር ዝንባሌ አለን፤ ነገር ግን ፈጣን ለዉጥ ሳናይ ስንቀር በችግሮቻችን ላይ የእግዚአብሔርን ቃል መናገር ትተን የስሜታችንን መናገር እንጀምራለን፡፡ ጽናት ድል ለማግኘት ወሳኝ አገናኝ ነዉ፡፡

ቃሉን ያለማቋረጥ መናገር ኀይለኛና ችግሮቻችንንና አሉታዊ ሁኔታዎቻችንን ድል ለመንሳት አስፈላጊ ነዉ፡፡ ምን እንደምታምን እወቅ እስከመጨረሻዉም በእሱ ጽና፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ! በህይወቴ ላሉ ተራሮች ቀልህን በየእለቱ እንድናገር አሳስበኝ፡፡ ተስፋ መቁረጥና ምሬት በሚገጥመኝ ጊዜ ሁሉ በአንተ ተማምኜ በተራሮቼ ላይ ቃልህን በድፍረት ተናግሬ እንዳንቀሳቅሳቸዉ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon