
እንግዲህ ወልድ ነጻ ካወጣችሁ፣በእውነት ነጻ ትሆናላችሁ፡፡ – ዮሀ 8፡36
እግዚአብሔር በምንም አይነት እስራት ውስጥ እንድንኖር ካልፈጠረን ፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዘንድ የሰጠንን ሁሉ እንድንደሰትበት ነጻነትን መለማመድ እንችላለን፡፡ ህይወትን ሰጥቶናል ፤ የእኛ ግብ ሊሆን የሚገባው በህይወታችን መደሰት ነው፡፡
በህይወታችን ነጻ መሆንን ብቻ መመኘት ብቻ አይበቃም፡፡ እርምጃም መውሰድ አለብን፡፡ የእግአዚአብሔርን ቃል መታዘዝ እና የመንፈስ ቅዱስን ምሪት መከተል ለእኛ አስፈላጊ ነው፡፡ ይሄም ማለት ውጤት ለማግኘት ቃሉን መስማት ወይም ማንበብ ብቻ ሳይሆን የሚለውንም ማድረግ አለብን፡፡
በህይወታችሁ ውስጥ ነጻነትን እየተለማመዳችሁ ነው? በኢየሱስ የእናንተ የሆነውን ነጻነት እንድትፈልጉ እግዚአብሔር ያበረታታችሁ ዘንድ እጸልያለሁ፡፡ ምክንያቱም በመስቀል ላይ የሞተው ከሀጢያት ሀይል ነጻ ሊያወጣን ነው፡፡ እኔ እና እናንተ ከማናቸውም አይነት በህይወታችን ካለ ችግር ነጻ እንድንሆን ነው፡፡
ነጻነት የእናንተ ነው ፣ አሁን ውጡና ውሰዱት፡፡ መንፈስ ቅዱን በመከተከል እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ያለውን ሁሉ ለመጠቀም ነጻ ሁኑ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ከማናቸውም አይነት ሀጢያት ፣ እስራት እና ጥቃት ነጻነቴን አግኝቻለሁ፡፡ በህይወቴ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በመከተል ለነጻነቴ እርምጃን መውሰድን መርጫለሁ፡፡