ለእናንተ የእግዚአብሔር ፍጹም እቅድ

ለእናንተ የእግዚአብሔር ፍጹም እቅድ

በእናንተ መልካምን ስራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው እርግጠኛ ነኝ፡፡ – ፊሊጲ 1፡6

ግዚአብሔር ለህይወታችሁ ፍጹም እቅድ አለው!” እኛ ሁላችን ይሄንን ሀረግ ሰምተነዋል ነገር ግን ብዙዎቻችን የምናምነው አይመስለኝም፡፡ምናልባት የሚያስቸግረን ቃል “ፍጹም” የሚለው ሳይሆን አይቀርም፡፡ማንም ፍጹም አይደለም እናም ፍጹም የመሆን ሀሳብ እራሱ ህይወታችን ላይ ጫና እና ጭንቀትን ነው የሚጨምረው፡፡

ፍጽምና የማይቻል ነገር ነው የሚመስለው። ምን ይመስላችኋል? እውነት ነው!

የእግዚአብሔር እቅድ ፍጹም ያልሆነው እኛ ፍጹም ስለሆንን አይደለም፡፡ እቅዱ ፍጹም የሆነው ያቀደው እግዚአብሔር ስለሆነ ነው፡፡ ፍጽምና የመጣው ከእርሱ ነው እናም እርሱ ብቻ ፍጹም ነው፡፡ ራሳችንን ከምናውቀው በላይ እርሱ ያውቀናል እና በተለይ ለእኛ ብቻ የተሰራ እቅድ ጨርሶ ተግባሩን ጀምሯል፡፡

ጳውሎስ በፊሊጲሲዩስ 1፡6 ላይ ሲናገር እግዚአብሔር አድኖን በእኛ መልካሙን ስራውን ጀምሯል እናም በእኛ ውስጥ ያለው ስራው ወደፍጻሜ ይመጣል፡፡

እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ በስራ ላይ እንደሆነ ስናስብ እኛ ፍጹም ባንሆንም እግዚአብሔር ፍጹም እንደሆነ ራሳችንን ማስታወስ ይኖርብናል፡፡ምንም አይነት የምናደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ፍጽምና ሊያረካ አይችልም፡፡ ኢየሱስ፣ ፍጹሙ ብቻ ነው ብቁ የሆነው፡፡ በክርስቶስ ስለሆንን የእግዚአብሔር ፍጹም እቅድ ለኛ ይቻለናል!


የጸሎት መጀመሪያ

ውድ ጌታ ሆይ ፍጹም እንዳልሆንኩ አውቃለሁ፡፡ነገር ግን ለእኔ ያለህ እቅድ የተመሰረተው በእኔ ሳይሆን በአንተ ፍጽምና ላይ ስለሆነ አመሰግናለሁ፡፡ በእኔ ውስጥ መልካም ስራን እያሳደክ ስለሆነ አመሰግናለሁ፡፡ እንደምትፈጽመውም አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon