ለኩነኔ አልተሰሩም

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፤ – ሮሜ 8፡1

በእየአንዳንዱ ጉባኤ ላይ ተገኝቼ ምን ያህል ሰው በኩነኔ ውስጥ እንደሚኖር በምጠይቅበት ጊዜ ባለማጋነን እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት እጃቸውን ያወጣሉ፡፡ እኔ ለኩነኔ እንዳልተሰራሁ እስካውቅ ድረስ እኔም ከእነዚህ እንደ አንዱ ከ80 በመቶዎቹ መካከል አንዱ ነበርኩኝ፡፡

እግዚያብሔር የኩነኔ ምንጭ አለመሆኑን በጣም ለበርካታ ጊዜያት መፅሃፍ ቅዱሴን በማጥናት እና ስለእሱ ባህሪ በማጥናት መረዳት ችያለሁ፡፡

ኩነኔ ህገወጥ የሆነ አዕምሯችንን የሚያጠቃ የጠላት መሳሪያ እንደሆነ አድርጌ አየዋለሁ ዓላማውም እግዚያብሔር በሰጠን ነገር መደሰት እንዳንችል ነው፡፡ ኩነኔ በእኛ ህይወት ውስጥ ምንም ስልጣን የለውም ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ዕዳችንን ከፍሎልናልና፡፡ በእኛ ላይ ህጋዊ ካልሆነ ወደ መጣበት ልንሸኘው ይገባል፡፡

ኩነኔ ደስታችሁን እንዳይሰርቃችሁ መከልከል አለባችሁ፡፡ማስታወስ ያለባችሁ እናንተ ለኩነኔ አለመሰራታችሁን ነው፡፡ በማንኛውም ጊዜ ይህን መሰል ነገር ሲሰማችሁ የእግዚያብሔርን ፍቅርና ፀጋ እንደተቀበለ ሰው በኃይል አታስተናግዱት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ለኩነኔ እንዳልተሰራሁ አውቃለሁ ፤ ኩነኔ በሚፈጠርብኝ በማንኛውም ጊዜ ይቅር የተባለኩ መሆኔን እና በክርስቶስ መስዕዋት ሙሉ እንደተደረኩኝ አስታውሰኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon