ለጠላቶችህ ምሕረት አሳይ

ለጠላቶችህ ምሕረት አሳይ

ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም። ማቴዎስ 5፡43 – 44

‘El Cid” የሚባለውን ፊልም እወደዋለሁ። ስፔይንን አንድ ያደረገ የጀግና ሰው ታሪክ ነው።

ለመቶ አመታት ክርስቲያኖች ከሙሮች ጋር ጥል ነበራቸው። እርስ በእርስ አይዋደዱም ነበር እርስ በእርስም ይገዳደሉ ነበር። በጦርነት ላይ እል ሲድ አምስት ሙሮች በቁጥጥር ስር አውሎ ግን ለመግደል ፈቃደኛ አልነበረም ምክንያቱም መግደል ምንም ጥሩ ነገር አምጥቶ እንደማያቅ ስለገባው ነው። ለጠላቶቹ ምህረት ማድረግ ልባቸውን እንደሚቀይር እና ሁለቱም ቡድኖች በሰላም መኖር እንደሚያስችል ያምን ነበር።

ከተያዙት ሙሮች መካከል አንዱ ” ማንም መግደል ይችላል ነገር ግን እውነተኛ ነጉስ ነው ለጠላቶቹ ምህረት የሚያደርገው” ብሎ ተናገረ። ኤል ሲድ ባደረገው አንድ ደግ ስራ ጠላቶቹ ራሳቸውን እንደ ጓደኛነት እና እንደ አጋርነት አቀረቡለት።

እየሱስ እውነተኛ ንጉስ ነው። ለሁሉም ለሚጠሉት ቢሆንም ጥሩ፣ደግ እና ምህረተኛ ነው። እኛ የእርሱን ምሳሌ ከመከተል በታች ማደረግ እንችላለን? በአሁኑ ጊዜ ምህረት ልታደርጉለት የምትችሉት ሰው ማሰብ ትችላላችሁ? ምህረተኛ እና ጥሩ መሆን በተለይ ለጠላቶታችን ማድረግ ከምንችላቸው ነገሮች መሃከል በጣም ህያሉ ነው።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሄር ሆይ ፤ ቀላል አይደለም ፣ ነገር ግን ጠላቶቼን ጨምሮ ለሁሉም ምህረት ማሳየት የምችል አይነት ሰው ምውሆን እፈልጋለሁ። አንተ ፀጋ ፣ የምህረት ሕይወት ለመኖር መረጥኩ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon