ለፍርሃት አትንበርከክ

ለፍርሃት አትንበርከክ

እኔ ግን ፈራሁ እና በአንተም ታመንኩ ፡፡ – መዝሙር 56:3

ፍርሃት ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን ነው፡፡ ስለዚህ በህይወትህ ፍርሃት ሲሰማህ ጠላት በናንተ ላይ እየመጣ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳስተምር ፍርሃት መንፈስ ነው እላለሁ፡፡ ፍርሃት ሰይጣን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለመቆጣጠርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመራር ስር እንዳይመላለሱ ለማድረግ የሚጠቀምበት መንፈስ ነው፡፡

በርካታ ሰዎች እግዚአበሔር በሕይወታቸው ላይ ያለውን ጥሪ የማይፈፅሙበት ምክንያት ወደፊት መራመድ ሲፈልጉ ሰይጣን ፍርሃትን በማምጣት ስለሚያስቆማቸው ነው፡፡ አንተን ለማስቆም ሰይጣን ፍርሃትን ተጠቅሞ ያውቃል? ሰዎች በሕይወት መደሰት እንዳይችሉ ሰይጣን ፍርሃትን ይጠቀማል፡፡ ፍርሀት ሥቃይ ያስከትላል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ በሕይወት ልትደሰትና ልትስቃይ አትችልም፡፡

ሰይጣን ፍርሃትን ሲያመጣባችሁ ጉልበታችሁን ለዚህ ፍርሃት ላለማንበርከክ መምረጥ ትችላላችሁ፡፡ ዳዊት ‹‹በፈራሁ ጊዜ በአንተ ታመንሁ›› ይላል፡፡ በሙሉ ልብህ እግዚአብሔርን መከተል በምትጥርበትና እርሱንም በምትከተልበት ጊዜ ጠላት በፍርሃት እንደሚያጠቃህ አምናለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ድፍረትህንና መተማመንህን በእግዚአብሔር ካደረግህ ግን ፍርሃትህን አሸንፈህ ወደፊት እንድትጓዝ ይረዳሃል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ለፍርሃት መንበርከክ አልፈልግም፡፡ ድፍረቴንና እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡ ፍርሃት መቋቋም የምችልበትን ድፍረትና አቅም እንደምትሰጠኝ በአንተ እተማመናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon