ሌላ ምንም የሚያረካህ የለም

ሌላ ምንም የሚያረካህ የለም

«… ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች» (ኢሳ.26፡9)።

ይህቺ ዓለም በቀላሉ ጆሮችን ለእኛ ቀላል በሆኑ ሁሉም ዓይነት ነገሮች በመሙላት የእግዚአብሔርን ድምጽ ከመስማት ውጪ ያደርገንና ህይወታችንን ከእርሱ በብዙ ርቀት እንድንርቅ ያደርገናል። ይሁንም እንጂ እግዚአብሔር ግን ጸንቶ ሲኖር ለሁሉም ሰዎች ቀን ይመጣል። ሌሎች ሁሉም ነገሮች በመጨረሻ ያልፋሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ አሁንም ጸነቶ ይኖራል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለእግዚአብሔር ሊታወቅ የሚገባው ሁሉ ግልጥ ሆኖ የሚታይ ነው ምክንያቱም እርሱ ራሱን በሰው ልጆች የውስጥ ህሊና የሚታወቅ አድርጓልና (ሮሜ 1፡19-21)። እያንዳንዱ ሰው በእርሱ ፊት በመቆም ለህይወቱ (ቷ) በእግዚአብሔር ፊት መልስ ይሰጣል (ትሰጣለች) (ሮሜ 14፡12)። ሰዎች በራሳቸው ህይወት እግዚአብሔር ለማገልገል ሳይፈልጉ ሲቀር፣ በራሳቸው መንገድ መመላለስን ሲፈልጉ፣ እንርሱም ራሳቸውን ከፈጣራቸው ለመሰወር መንገድ ሲፈልጉና የውስጥ የደመነፍስ ዕውቀታቸውን ቸል ይላሉ፣ እነርሱ ሊሄዱበት የሚገባውን መንገድ ል ሊናገራቸውና ሊመራቸው ይፈልጋል።

እውነቱ ይህ ነው፣ ከእግዚአብሔር ለመሰወር ሞክሩ ወይም አይሞክሩ ከእርሱ ጋር ህብረትና ግንኙነት ካላደረግን በስተቀር ውስጣዊ ናፍቆታችንን ሊያረካን የሚችል ምንም ነገር የለም። ሰዎች እንኳን ቸል ቢሉትም ሰዎች እርሱን ለመስማት በጥልቅ ፍላጎት እርሱን ድምጽ ለመስማት ይወዳል።

እኔም የማበረታታህ ከእርሱ ጋር ጊዜ በማሳለፍ፣ በህልውናው ውስጥ በመቆየትና የእርሱን ድምጽ በመስማትእግዚአብሔርን የሚናፍቀውን መሻትህ ታሟላለህ።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ በምድር ላይ ያለው ህይወትህ በሚያልፍበት ጊዜ ህይወትህን ፍርሃትና ስጋት በሌለበትሁኔታ በእግዚአብሔር ፊት ኑረው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon