ልሁቅ ሁን

‹‹ … ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም›› (1ኛቆሮ.6፡12) ።

እግዚአብሔር በብዛትና በተትረፈረፈ በረከቶች ሊባርከን የሚያስደንቅ እቅድ አለው፡፡ ነገር ግን በእርሱ ዕቅድ በሙላት ለመደሰት በብዛትና ከመጠን በላይ ለእርሱ መታዘዝ አለብን፡፡ በእርሱ የበረከት መንገድ ውስጥ ለመኖር የእግዚአብሔር እርዳታ ያስፍልገናል፡፡ በህይወትህ ውስጥ እርሱን የማያስደስት የህይወት ክፍል ካለ እርሱ ከአንተ ጋር በጽናት እንዲሞግት ጠይቀው፤ እርሱ ይህንን ሲያደርግ በፍጹምና በፍጥነት በመታዘዝ ምላሽ ስጥ፡፡

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በውስታችን ያስቀመጠው በፍጹም ሰላም ሊመራን ነው፡፡ እኛ እርሱን የምንሰማው ከሆነ ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰንና በእርሱ ሰላም ደስተኛ እንሆናለን፡፡ በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምንመለከተው ሁሉም ነገረር ተፈቅዶልናል፡፡ ነገር ግን ሁሉም የሚጠቅመን አይደለም፡፡ እናም ማንኛውንም ነገር ህይወታችንን የሚቆጣጠረን ምክንያት እንዲሆን መፍቀድ ሞኝነት ነው፡፡

ብዙ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ፤ ነገር ግን እነርሱ ሁሉም በህወታችን ዋና አይደሉም ወይም መልካም ውጤት የሚስገኙልን አይደሉም፡፡ ጳውሎስ ከሁሉም የሚልቀውን ነገር መምረጥና ዋጋ መስጠት አለብን ይላል (ፊል. 1፡10) ፡፡ እግዚአሔር በምናደርጋቸው ማናቸውም እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ መለኮታዊ ቃል አይሰጠንም፤ ነገር ግን እርሱ ቃሉንና ጥበቡን አንድንኖርበት ከእኛ እየጠበቀ ይሰጠናል፡፡ ወላዋይ አትሁን እንዲሁም በእርሱ አንድ ነገር ለማግኘት ተስፋ አታድርግ፤ ነገር ግን በዚህ ፈንታ የላቀውን ነገር መምረጥና እግዚአብሔርን ደስ የምታሰኝበትን እወቅ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ የላቁ ምርጫዎች የላቁ ሽልማቶችን (ውጤቶችን) ያመጣል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon