“ልማዳዊ” ነገሮችን መቀደስ

ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።ሮሜ 145

እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርትነታችን ሁለንተናችንን ለእግዚአብሔር መስጠትና እርሱን  በሁሉም ነገራችን ማስደሰት አለብን (ቆላ 1፡10)፡፡ ልማዳዊ፣ የየዕለት ሀላፊነቶቻችንን ከመንፈሳዊ ነገር ነጥለን ከእግዚአብሔር ጋር ትክክል የሚያደርጉንና ቅዱስ አድርገን የማየት ዝንባሌ የለንም፡፡

ይህንን ልንረዳ ያስፈልጋል፤ በአእምሮአችን ዉስጥ ካልሆነ በስተቀር በእዉነታዉ ልማዳዊና ቅዱስ የሚባል ነገር የለም፡፡  ማንኛዉም ነገራችን ለጌታ መቅረብ አለበት ይህንንም በንጽህ ልብ ካደረግነዉ ቅዱስ ነዉ፡፡ ልክ ሱቅ እንደመሄድ ያሉ ልማዳዊ ነገሮችን ልታደርግ ትችላልህ ይህንን ለእግዚአብሔር ክብር እስካደረግህ ድረስ ልክ እንደ ጸሎት ቅዱስ ተግባር ነዉ፡፡

በዚህ ነገር ነጻነት ለማምጣት ሮሜ 14 እጅግ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነዉ፡፡ በእኔ የግል ትርጉም ቁጥር 5 እና 6 አንድ ሰዉ ጸሎትንና የቃል ጥናትን ከሌሎች የየዕለት ስራዎች ይልቅ ቅዱስ ነገር አድርጎ ሲመለከት በጌታ ነጻ የሆነ ሰዉ ደግሞ ሁሉንም ነገር ቅዱስ አድርጎ ያያል ምክንያቱም ማንኛዉም የምያደርገዉ ነገር ለጌታ ክብር ነዉና፡፡

ለእግዚአብሔር ግማሹን የህይወትህን ክፍል በመስጠት ፈንታ የምታደርገዉን ሁሉ እርሱን ለማክበር ለማድረግ ምርጫ አድርግ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ህይወቴ በጠቅላላ ቅዱስ እንዲሆን እፈልጋለሁ፤ የየቀኑን እንቅስቃሴዬን ለአንተ አቀርባለሁ አንተን ለማክበርም እኖራለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon