ልምምድ ውጤታማ ያደርጋል

ልምምድ ውጤታማ ያደርጋል

አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉ እርሱንም ፍራ፣ ትዕዛዙንም ጠብቁ፣ ቃሉንም ስሙ እርሱንም አምልኩ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ፡፡ ዘዳ 13÷4

አንደዚ እግዚአብሔርን ማድመጥና ከእርሱ መስማት ከጀመርን ምንም ቢሆን ያዘዘን ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ መታዘዛችን ከእርሱ ጋር ያለንን ሕብረትንና እምነታችንን ያጠነክራል፡፡ ከእርሱ መስማትና መታዘዝ ስንቀጥል፤ ልምምድ ውጤታማ በእውነት ያደርጋል ማለት እንጀምራለን፡፡ በሌላ አነጋገር ልምምድ ባገኘን መጠን መተማመናችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ምርትና መታዘዝ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለመግባት ብዙ ልምድ ይጠይቃል፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማና መንገድ ሁልጊዜ መልካምና የሚያዋጣ ልምምድ ይጠይቃል፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማና መንገድ ሁልጊዜ መልካምና የሚያዋጣ ብናውቅም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የግል መስዋትነት የሚጠይቁ ነገሮችን ሲያዘን ችላ እንላለን ወይ ደግሞ በትክክል ከእግዚአብሔር ለመስማታችን ፍርሃትና ጥርጣሬ ውስጥ ስለምንገባ እርምጃ ለመውሰድ እንፈራለን፡፡

ዋጋ ወይም መስዋዕት ለመክፈልና ለመሳሳት መፍራት የለብህም፡፡ በሕይወት ገጠመኞች ውስጥ ብዙ የከፉ ነገሮች ከስህተቶቻችን ይበልጣሉ፡፡ እየሱስ ‹‹ተከተለኝ›› አለ፡፡ እኔ በእርግጥ የማምነው ከእግዚአብሔር ለመስማት የራሳችን ድርሻ ስንወጣ የነገሩን አካሄድና ውጤት በእርጋታና በትክክል ከእግዚአብሔ ለመስማታችንና ላለመስማታችን ማየት አለብን፡፡ በፍርሃት መሸማቀቅ በሕይወታችን ዘመን ሁሉ ከእግዚአብሔር ለመስማት ያለንን ችሎታና እድገት ይገድብብናል፡፡

‹‹አንተ መሪውን ያዝ እኔ እከተልሃለሁ›› አላለም፡፡ እግዚአብሔር ያለን በችኩል በጥሩ ሁኔታ እንኳ ብንሠራው እርግጠኛ ነኝ ሕይወታችን የተመሰቃቀለ ይሆናል፡፡

ልጆቻችን በእግራቸው ለመራመድ በሚያደርጉት ጥረት ወድቀው ሲነሱ አንናደድባቸውም፡፡ ትክል እንደሆኑና እየተማሩና እየተለማመዱ እንደሆነ በማወቅ እናግዛቸዋለን፡፡ ልክ እግዚአብሔም እንደዛው በእምነትና ያለፍርሃት ሆነ እንድትሰማው ያስተምርሃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔርን አድምጥ (ስማ)፣ ድምፅን ለይ፣ በእርግጠኝነት ታዘዘው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon