ልባችሁን መጠበቅ

ልባችሁን መጠበቅ

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤የህይወት ምንጭ ነውና፡፡ – ምሳሌ 4፡23

ምሳሌ 4፡23 ልባችንን መጠበቅ የህይወታችንን አካሄድ የሚወሰነው መሆኑን ይነግረናል፡፡አስቡበት፡፡በልባችሁ ያለው ማናቸውም ነገር በየዕለት ተዕለት ህይወታችሁ መገለጡ አይቀርም፡፡ውስጥ ያለው ማንኛውም ነገር ሁሉም ሰው እያየው መውጫ መንገድ ማግኘቱ አይቀርም፡፡

ይሄ ብቻውን ልባችንን ቅርጽ እንዲያስይዙት የምንፈቅድላቸውን ነገሮች በጥንቃቄ መቆጣጠራችን ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል፡፡የሆነ ትክክል ያልሆነ፣ሀጢያት የሆነ እና ራስ ወዳድነት ያለበት ከልቤ ወጥቶ ግንኙነቶቼን እንዲያበላሽብኝ አልፈልግም፣ እናንተም እንደማትፈልጉ ነው እርግጠኛ ነኝ፡፡

አብዛኛው ልብን የመጠበቅ ትረጉም የሚያተኩረው ሀሳባችሁን፣ቃላታችሁን፣አደራረጋችሁን እና አጠቃላይ አመለካከታችሁን በመጠበቅ ላይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የምታስቡት ነገርበንግግራችሁ ይወጣል፡፡የምትናገሩት ደግሞ ከስሜታችሁ ጋር ይያያዝና በአጠቃላይ አመለካካታችሁ ላይ ይንጸባረቃል፡፡

በየዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ውስጥ ሁኔታዎችን እንዴት እንደምታስተናግዷቸው፤በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ሰላም ትሆኑ ወይም ትሰባበሩ እንደሆን የሚወስነው ይሄ ነው፡፡በተለይ ከነሱ ጋር ባልተስማማችሁበት ጉዳይ ላይ ለሌሎች የምትመልሱት በርህራሄ እና በመረዳት ይሁን በፍርድ እና በግትርነት የሚወስነው ይሄ ነው!

በውስጣችሁ የምታስቡት ነገር ቃላቶቻችሁንና አመለካከታችሁን እንዳይለውጡት ለመጠበቅ መሞከር ትችላላችሁ፤ነገር ግን እኔ ለመጀመር እግዚአብሔራዊ አመለካከቶች ሲኖሩን የሚቀል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ጊዜ አሳልፉ እና መንፈስ ቅዱስ በመልካምነት ልባችሁን እንዲሞላው ፍቀዱለት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ልቤ እንዲሞላ የምፈልገው ከአንተ በሆኑ ሀሳቦችና መሻቶች ነው፡፡በህልውናህ ውስጥ ብዙ ጊዜ ሳሳልፍና በአንተ ላይ ባቻ ሳተኩር ልቤ ለመልካም እንደሚቀየር እናም በእግዚአብሔርዊ መንገድ ቀሪውን ህይወቴ እንደሚነካ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon