ሐቀኝነት ከፍጽምና የበለጠ አስፈላጊ ነው

ሐቀኝነት ከፍጽምና የበለጠ አስፈላጊ ነው

ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:2

ሰዎች ለእኛ ያላቸው አስተሳሰብ አስሮ አስኪያስቀምጠንና በፍርሃት እስኪውጠን ድረስ ቦታ ልንሰጠው እንችላለን። ይህንን ታውቃላችሁ? እንደሚመስለኝ ከሆነ ጥፋት የሌለብን ለማስመሰል ሁሉንም ነገር ከመደበቅ ይልቅ እውነተኛ ብንሆን የበለጠ ክብር እናገኛለን።

ሰዎች እኔን ማዳመጥ የሚወዱበት ዋነኛ ምክንያት ነው ብየ የማስበው በራሴ ችግር ፣ ድክመት እና ጥፋት ላይ የተማርኩትን ስለማካፍል ነው ብየ አስባለሁ። ዘና እንዲሉ እንዲሁም እኔ እንዳደረኩት ሲያውቁ እነሱም ማድረግ እንደሚችሉ ተስፋ ይሰጣቸዋል።

ጥፋት እሰራለሁ ብሎ በፍርሃት መኖር ማቆም አለብን ምክንያቱም ጥፋት መስራታችን አይቀርም ፤ በቃ! እግዚአብሄር ጥፋት እንዳንፈፅም አልጠየቅንም። የጠየቀን ስለጉድለታችን ግልፅ እና እውነተኛ እንድንሆን ነው። ይህንን በምናደርግ ግዜ እርሱ ያስወግድልናል ወደተሻለም ነገር ይመራናል።

ጥፋቶቻችሁን አትደብቁ። ከነሱ መማር ትችሉ ዘንድ በግልፅ አውጧቸው። እግዚአብሄርን ግልፅ እና እውነተኛ ሆናችሁ ስታምኑት ማንኛውንም ነገር ለማለፍ ይረዳችኋል።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ፤ የማፍርበት ድክመት አለኝ። እነሱን ይዤ መቆየት እንደማይጠቅመኝ አውቃለሁ። ድክመቶቼን መወጣት ትረዳኝ ዘንድ ግልፅ ለመሆን ወስኛለሁ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon