እንደ አንድ አካል ሆናችሁ የተጠራችሁበት የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገስ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ፡፡ – ቆላ 3፡15
ሁላችንም ስሜቶች አሉን መኖርም አለባቸዉ፡፡ የእያንዳንዱ አማኝ አንዱ ግብ ስሜታዊ መረጋጋት ወይም መስከን እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ስሜቶቻችን እኛና ሳይሆን እኛ ስሜቶቻችንን እንዴት መግዛት እንዳለብን እንድንማር እግዚአብሔርን መጠየቅ አለብን፡፡
ይህንን አስብ፤ አንዳች ያስፈለገህን ነገር ለመግዛት ሸመታ ወጥተሃል እንበል፤ ዕዳ ዉስጥ እንዳትገባ በጌታ ፊት ወስነሃል ደግሞም ከአቅምህ በላይ ላለመሸመት ወስነሃል ነገር ግን እዚያ ሱቅ ዉስጥ የ50 በመቶ ቅናሽ እንደተደረገ አየህ፡፡ ምን ታደርጋለህ? ስሜትህን ተከትለህ ትሸምታለህ ወይስ ለመወሰን ስሜትህ እስኪሰክን ትጠብቃለህ?
እግዚአብሔር በሰላም የተገዛ ዉሳኔ እንድትወስን ነዉ የሚፈልገዉ፡፡ የእርሱ ሰላም ሁሌ እንዲገዛህ መፍቀድ ማለት ስሜቶችህ እስኪሰክኑ መጠበቅና ከዚያ ፈትሾ ያመንኩበት ትክክል ነዉ ወይ ብሎ ማድረግ ነዉ፡፡
ስሜቶችህ እንዲወስኑ አትፍቀድ፡፡ ዘወትር በሰላም ተመላለስ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! ሰላምህ በልቤ እንዲገዛ መርጬአለሁ፡፡ በስሜት ተነድቼ መወሰን አልፈልግም ይልቅ ስሜቴን ገርቼ እንሄድበት የወሰንከዉን የሰላም ጎዳና እጓዛለሁ፡፡