መለኮታዊ አንቀሳቃሽ

መለኮታዊ አንቀሳቃሽ

አቤቱ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ ፤ – መዝሙር 139፡23

ከዓመታት በፊት በገንዘብ አቅራቦት ትግል ውስጥ በነበርንበት ወቅት ፣ በእመነቴ ደክሜ እና ለጥርመሳ የሚሆን መታመን ከብዶች በጌታ ፊት ተደፋሁ፡፡ ለተወሰኑ ጊዚያት አለቀስኩኝ ፤ከዛ በኋላ ግን በእግዚአብሔርም ጸጋ ውሳኔን ወሰንኩ ‹‹ እግዚአብሔር ሆይ እስክሞት ድረስ በመስጠቴ የሚመጣ ነገር ቢኖርም ባይኖርም አስራቴን አወጣለሁ ፤ መባም እሰጣለሁ›› ብዬ አዋጅን አወጅኩ፡፡

ይህ ለእኔ በሙሉ ልቤ ለምን መስጠት እንዳለብኝ እና እሰጥ ይሆን የሚል ፈተናዬ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በእርግጥ ትክክለኛ አንቀሳቃሽ ምክንያት እንዳለኝ መግለጽ ፈልጎ ነበር፡፡ ‹‹ለመቀበል መስጠት›› በሚል አድርጌው ቢሆን ምናልባት ከራስ ወዳድነት ከእግዚአብሔር አንዳች ለማግኘት ነበር የምሰጠው፡፡

በርካታ ስብከቶች እና ትምህርቶች ‹‹ይህንን ብታደርግ ይህ ይሆንልሃል›› የሚሉ ናቸው ነገር ግን ንጹ ልብ ካለን ‹‹ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ እፈልጋሁ ምክንያቱም ትክክለኛ እና እግዚአብሔርን የሚያከብር መሆኑ ነው››;

ዛሬ በምን ዓይነት የውስጥ አንቀሳቃሽ እንደምትንቀሳቀሱ ራሳችሁን እንድትመረምሩ አበረታታችኋለሁ ፤ ለራስ ጥቅም እንዳልሆነ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ለትክክለኛው ምክንያት ለእግዚአብሔር አገልግሎት በሙሉ ልብ የሚደረግ መሆኑን ልብ አደርጉ፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ልቤን መርምር እና በውስጤ ያለውን አንቀሳቃሽ ሰበብ እና የውስጥ ፍላጎቴን ግለጠው፡፡ መለኮታዊ ያልሆኑ እንደሆነ ጠቁመኝ እንዲለወጡም እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon