መልካሙን ገድል እንዴት እንጋደል

መልካሙን ገድል እንዴት እንጋደል

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መጋደል የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ፡፡ – 1 ጢሞ 6:12

ጠላታችን ጋር መልካሙን የእምነት ፍልሚያ መፋለም አለብን ነገር ግን ያ ፍልሚያ በተግባር ምን ይመስላል? እዚህ 6 ቁልፍ ዘዴዎች አሉ፡፡

  1. በኃይል አስብ፡ ልክ ለዉጊያ እንደሚዘጋጅ፣ እንደሚያቅድ እና እንዴት እንደሚገጥምና ድል እንደሚነሳ እንደሚያሰላ የጦር አዛዥ፡፡
  2. ከልብ ጸልይ፡ ዕብራዊያን 4፥16 የሚያዘን ወደ እግዚአብሔር ዙፋን በድፍረትና በልበሙሉነት እንድንቀርብ ነዉ፡፡ ወደ እርሱ በድፍረት ቅረብና የሚያስፈልግህን ጠይቀዉ፡፡
  3. ያለ ፍርሃት ተናገር፡ 1ኛ ጴጥ 4፥11 ከእናንተ ማንም የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር እንዲል፤ እናንተና እኔ በክፉዉ ሐይል ላይ የማዘዝ መንፈሳዊ ድምጽ አለን፡፡
  4. አብዝተህ ስጥ፡ የምንሰጥበት መንገድ የምንቀበልበትም መንገድ ነዉ (ሉቃ 6፥38ን ተመልከት)፡፡ የለጋስነት ሕይወት ኑር፡፡
  5. በጥንቃቄ ሥራ፡ ምንኛዉንም እጅህ የሚያርፍበትን ነገር በሙሉ ሐይልህ ልትሰራ ያስፈልጋል (መክብብ 9፥10) በመንፈስ ቅዱስ ላይ ተደገፍ ሥራዉ ተጠናቆ ተቀበል፡፡
  6. ያለቅድመ ሁኔታ ዉደድ፡ እንደ እግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር እንደወደደን ሌሎችን ያለ ቅድመ ሁኔታና በመስዋዕትነት እንዉደድ፡፡

እነዚህን ደረጃዎች ያዝ እና ጠላት ሲመጣብህ በእግዚአብሔር ሐይል ትሞላለህ የማትመታም ትሆናለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ኋላ መቀመጥና እንድጋደለዉ የጠራሀኝን የእምነት መጋደል ማጣት አልፈልግም፡፡ ወደ ፊት በተጓዝኩ ቁጥር ከጠላት ጋር በሚኖረኝ ዉጊያ እነዚህን 6 ዘዴዎች እንዴት መተግበር እንደለብኝ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon