መልካምን ለማድረግ “መፈተን”

መልካምን ለማድረግ “መፈተን”

ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። – 1 ቆሮ 10፡12

አንዱ ኀጢአት ወደ ማድረግ ፈተና የሚገፋን ነገር ስለራሳችን አብዝተን ማሰብና ራሳችንን አብዝተን ማመናችን ነዉ፡፡ ይህ በጠላት የሚበረታታ አመለካከት ነዉ፡፡ በኩራት ተሞልተን ደህና እንደሆንን እናስብ ይሆናል ከዚያም ሰይጣን ይፈትነናል በኀጢአትም እንወድቃለን፡፡

የሚቀጥለዉ አረፍተ ነገር ሊያስደነግጥይ ይችላል፤ መልካም ዓይነት ፈተናም እንዳለ ማወቅ አለብህ፡፡ ሰይጣን ክፉ እንድንሰራ እንደሚፈትነንና እግዚአብሔርም መልካም እንድናደርግ እንደሚፈትነን መገንዘብ ያስፈልገናል፡፡ ሁል ጊዜ ሰይጣን ከፊትህ ክፉ አማራጮችን ሲያስቀምጥ እግዚአብሔር ደግሞ መልካም አማራጮችን ያዘጋጃል፡፡

የኀጢአት ፈተና ሲያደክምህ ከጠላትህ በላይ ሐይለኛ የሆነዉን መንፈስ ቅዱስ አስታዉስ እርሱ በመልካም መንገድ ያደክምሃል፡፡ ከፈቀድክለት ታላላቅ ነገሮችን እንድታደርግ ተጽዕኖ ያደርግብሃል፡፡

እግዚአብሔር ኑሮአችንን ለማዳን እየጣረ ነዉ፡፡ ምንም ቢፈጠር እንድንጸናና በእርሱ ጥላ ሥር እንድንጠበቅ ሊያበረታን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር መልካም ነገር እንድታደርግ ሲፈትንህ ማድረግ የምትችለዉ የተሻለዉ ነገር መታዘዝ ነዉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ! የአንተን መልካም “ፈተና” ማድመጥና መታዘዝ እፈልጋለሁ፡፡ ጠላት ሊያሸብረኝ ሲፈልግ መከተል ያለብኝን የፈቃድህን መንገድ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon