መልካም አንደበት

መልካም አንደበት

በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ (ኤፌሶን 5፡19)

የዛሬዉ ቃል በድሮዉ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም እንደዚህ ይላል፡- “በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፡፡” ይህን ቃል በሁለት መንገዶች መተግበር እፈልጋለሁ፡፡ ላራሴ የምናገርበት መንገድ አስፈላጊ ነገር ነዉ፣ ለሌሎችም የምናገርበት ነገርም እንደዚሁ፡፡

እራሳችን በምንናገራቸዉ መጥፎ ነገሮች፣ ችግሮች፣ ተስፋ መቁረጦች እና ፈተናዎች ተጠልፈን ወጥመድ ዉስጥ ለመዉደቅ ቀላል ነዉ፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ ነገሮች አንዱ እንኳ መንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ አያደርጉንም፣ የመንፈስ ቅዱስን ተግባርም አይገልጹም፡፡ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በፍጹም እንደዚህ አይነቱን ነገር አያደርግም፡፡ እሱ ስለ አንድ ችግር ሊናገረን ከፈለገም፣ ከመፍትሄዉ ጋር ነዉ፡፡ ስለችግር ሲነግረን፣ ጥንካሬዉንና ማጽናናቱን አብሮ ይልካል፡፡ ስለችግሮቻችን ማዉራታችንና ማሰባችን ሲበዛ፣ ድካማችን ይጨምራል፤ ይሁን እንጂ ስለኢየሱስና ስለገባልን ቃልኪዳን ካሰብንና ካወራን ጉልበታችን ይበረታል፡፡

ህይወት ሁል ጊዜ ቀላል አይደልም፡፡ ሁላችንም የተለያዩ ችግሮች በተለያዩ ጊዜያት ያጋጥሙናል፡፡ እግዚአብሔር የማይቻለዉን የምንችልበትን መንፈሱን ሰጥቶናል፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ብታልፍም፣ ጆሮህየእግዚአብሔርን ድምጽ እንዲሰማ ወደ እሱ አዘንብል፡፡ እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ የገለጠልህን መልካም ነገሮች ብቻ አዉራ፡፡ ሁላችንም የአንደበታችንን ፍሬ ስለምንበላ በህይወት የተሞላን ቃል በራሳችን ላይ መናገር ይገባናል፡፡”


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ንግግራችን የህይወትና የሞት ኃይል ስላላቸዉ፣ ዛሬ ንግግርህን በጥበብ የተሞላ እንዲሆን አድረገዉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon