መልካም የሆነዉ ሸክም

መልካም የሆነዉ ሸክም

ነገር ግን፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወደ ባሪያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፥ ዛሬም ባሪያህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን ስማ፤ (1ኛ ነገስት8፡28)

እንዳንድ ጊዜ ለሌሎች ሰዎች ስትፀልዩ ለሌሎች የመጸለይን ወይም የመማለድን ሸክም ተቀብላችኋል ማለት ነዉ፡፡ ሸክም አስፈላጊ ሆኖ ልባችሁ ላይ ከብዶ የሚመጣና የሚሰማ እግዚአብሔር በፀሎት እንድትሸከሙት የሚጠይቃችሁና ልትተዉት የማትችሉት ነገር ነዉ፡፡ እግዚአብሔር እንዳንድ ጊዜ ሊናገራችሁና ስለ ሸክሙ ሊገልጥላችሁ ይችላለል፡፡ አንዳንድ ጊዜ መጸለያችሁን እንጂ ሸክሙ ምን እንደሆነ እንኳን ላታዉቁትና ላትረዱ ትችላላችሁ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ስለአንዳንድ ጉዳዮች አብዝተዉ እንዲጸልዩ ተጠርተዋል፡፡ ባለቤቴ ለአሜሪካ ሀገር ብዙ ጊዜ ይፀልያል፡፡ ለእስራኤል አብዝተዉ የሚፀልዩ ሰዎች እንዳሉ አዉቃለሁ፡፡ አንዲት ሴትከጦር ሜዳ ለተመለሱወታደሮች ትጸልይ እንደነበረ ነግራኛለች፡፡ እግዚአብሔር በአለም ላይ ስላለዉ ጉዳይ ሁሉ እንደሚገደዉ አምናለሁ፡፡ ሁላችንም ተመሳሳይ ለሆነ ነገር መጸለይ የለብንም፡፡ እንደዛ ቢሆንማ ልንፀልይባቸዉ የሚገቡ ሌሎች ነገሮች ሳይፀለይላቸዉ ይቀራሉ ማለት ነዉ፡፡ እግዚአብሔር

እንድትፀልይበት ሸክም ለሰጠህ ጉዳይ ትኩረት ስጥና ጸልይ፡፡

እግዚአብሔር እኛን ከሚናገርባቸዉ መንገዶች አንዱ ስለሌሎች ሸክምን በሚሰጠን መንገድ በኩል ነዉ፡፡ የህንንም የሚያደርገዉ በቃል እየተናገረን ሳይሆን ሸክምን ዉስጣችን በማኖር ነዉ፡፡ ይህ ሲሰማን ለሌሎች እንድንፀልይ እየተናገረን ነዉ፡፡ እሱ ለሚሰጠን ሸክምና እንድናደርገዉ ለሚፈልገዉ ነገር ትኩረት እንስጥ ለመጸለይም ታማኞች እንሁን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ለሌሎች ስትጠልይ እግዚአብሔር ደግሞ ላንተ የሚጸልይ ሰዉ እንደሚያዘጋጅ ልብበል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon