መልካም ፍሬ አፍራ

ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀመዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከብራል፡፡ ዮሐ. 15÷8

በዛሬው ጥቅስ ውስጥ ኢየሱስ ፍሬ ስናፈራ እግዚአብሔር ይከብርበታል ነው ያለው፡፡ በማቴ 12÷33ም ስለ ፍሬ ስናገር ዛፎች ከፍሬአቸው ይታወቃሉ አለ፡፡ በማቴ 7 ÷15-16 ላይም ጨምሮ ተመሣሣይ መመሪያ ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህ ጥቅሶች የሚያመለክቱን እኛ እንደ አማኞች ግድ ሊለን የሚገባንን ምን ዓይነት ፍሬ እያፈራን እንደሆነ ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ የሆነውን መልካሙን ፍሬ ማፍራት እንዳለብን ነው፡፡ (ገላ 5÷22-23 ተመልከት) ነገር ግን ያንን እንዴት ነው የምናደርገው፡፡

እግዚአብሔር የሚያጠፋ እሳት እንደሆነ እናውቃለን እንዲሁም ኢየሱስም የተላከው እኛን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ሊያጠምቀን ነው፡፡ የእግዚአብሔር እሳት በሕይወታችን አንዳንድ እስካልፈቀደልን ድረስ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ በሕይወታችን ማየት አንችልም፡፡
መልካም ፍሬ ማፍራት የሚመስጥ ሊመስለን ይችላል ፍሬ ማፍራት መገረዝ እንደሚያስፈልግ እስክንረዳ ድረስ፡፡ ኢየሱስ ‹‹በእኔ እያለ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አብዝቶ ፍሬ እንዲያፈራ ይገርዘዋል፡፡ እንዲሁም በተከታታይ በመግረዝና በማጽዳት በተከታታይ ፍሬ እንዲያፈራ ያደርገዋል፡፡ የበለጠ እንዲያፈራና እንዲፋፋና የበለጠ ፍሬ እንዲፈራ (ዮሐ 15÷2 ተመልከት) ልክ እሳት እንደሚያደርገው የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በሕይወታችን ግዝረትን ያደርጋል፡፡ እሳት ለማንፃትና ሥጋን ለመግደል ይጠቅማል፡፡ ግዝረት ለእድገት ያስፈልጋል፡፡ የሞቱ ነገሮችና በተሳሳተ መንገድና አቅጣጫ የሚሄዱ ነገሮች ተቆርጦ ሲወገዱ ልክ እንደ ጽድቅ ዛፎች እናድግና ብዙ ፍሬ ለእግዚአብሔር እናፈራለን፡፡ (ኢሣ 61÷3)


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እግዚአብሔር ከሕይወትህ የሆነ ነገር ስቆርጥ እርሱ ሁልጊዜ በመልካም ነገር መኖሪያ ልያደርግህ ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon