መራርነት እርሱን እንዳንሰማ ያግዳል

መራርነት እርሱን እንዳንሰማ ያግዳል

«…መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ» (ኤፌ.4፡31) ።

መራርነት በእግዚአብሔር ፊት የእርሱን ድምጽ እንዳንሰማ በትክክል እንቅፋት ይሆንብናል። ሁልጊዜ መራርነት ከመልካም ነገር ሁሉ ሊያጎድለን ወይም ሊገድበን ይሞክራል፤ ተቃወመው። ብዙውን ጊዜ ዲያቢሎስ አንድ ወቅት የሆነብንን ክፉ ጊዜያት እያስታወስን እንድንቆዝም ሊያደርግ ይጥራል። ይህ ማለት ምንም የማናዝን ፍጡራን ነን ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ችግራችንን (መከራችንን) ምንም ያህል የከፋ ቢሆን ሌላውe ሰው ደግሞ ከእኛ እጅግ የከፋ ችግር ይኖረዋል፡፡

አንድ ለእኔ የምትሠራ ሴት ከሰላሳ ዘጠኝ ዓመታት የትዳር ህይወት በኋላ ትቷት ሄደ፡፡ እርሱም ትንሽ ማስታወሻ ጽፎ አስቀምጦላት ሄደ፡፡ ይህ ለእርሷ እጅግ አሳዛኝ ነበር፤ እርሷም ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወደ እኔ መጥታ ‹‹እባክሽ ጆይስ ጸልይልኝ፤ በእግዚእሔር ላይ ልቤ እንዳይነሳ፤ ሰይጣን በክፉ ሁኔታ በእግዚአብሔር ላይ እንድነሳሳ እየፈተነኝ ይገኛል፡፡ እኔ በእግዚአብሔር ላይ መነሳት አልችልም፡፡ እርሱ (ባለቤቴ) ብቸኛ ያለኝ ወዳጄ ነውና አፈልገዋለሁ፡፡›› ብላ ስተነግረኝ በጣም ተማመንኩባት፡፡

መራርነት በጓደኛዬ ልብ ውስጥ ሥር ለመስደድ ሞክሯል፡፡ ምክንያም ህይወቷ እርሷ ከምትፈልገው መንገድ አልተመለሰም፡፡ ስንጎዳ ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ነጻ ፈቃድ ያለው ሰው መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ በጸሎትም እንኳን ቢሆን ማንም ሰው ያንን የሰው ነጻ ፈቃድ መቆጣጠር አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ለጎዱን ሰዎች እንዲናገር መጸለይ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ክፉ ከማድረግ ፈንታ መልካም እዲያደርጉ እንዲመራቸው መጸለይ እችላለን፡፡ ነገር ግን ዋናው ጉዳይ እርሱ የራሳቸውን ምርጫ ያደርጉ ዘንድ ይተዋቸዋል፡፡ አንድ ሰው እኛን ሊጎዳን ከመረጠ እግዚአብሔር ላይ መቆጣት እና በእርሱ ላይ መራራ መሀን አይጠበቅበትም፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ስትጎዳ መቼም ቢሆን እግዚአብሔር ላይ አትቆጣእርሱ ለአንተ ከሁሉም የላቀ ወደጅe ነውና፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon