መስጠት ዋጋ ሊያስከፍል ይገባል

መስጠት ዋጋ ሊያስከፍል ይገባል

ንጉሱም ኦርናም ፡- እንዲህ አይደለም ፣ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም አለው፡፡ – 2 ሳሙኤል 24፡24

በእግዚአብሔር መግቦት ውስጥ ምንም አይነት ርካሽ ነገር ዋጋ የለውም፡፡ እግዚአብሔር ብቸኛ ልጁን ስለ እኛ ሰጠ ነጻ እንዲያወጣን፤ ምንም እንኳን የሚሰተካከል መስዋዕት ማድረግ ባንችልም ዋጋ ያለው ነገር ግን ለእርሱ ልናደርግ ይገባል፡፡ ንጉስ ዳዊት ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም አለ ፤ እኔ የተረዳሁት እውነተኛ መስጠት ፤ ስሰጥ ካልተሰማኝ መስጠት አንዳልሆነ ነው፡፡

የተጠቀምኩባቸውን አልባሳት እና የቤት ቁሳቁሶች መስጠት ምናልባት ጥሩ ምግባር ናቸው ነገር ግን ከእውነተኛ መስጠት ጋር አይተካከሉም፡፡ እውነተኛ መስጠት ልጠቀምበት ወይም እንዲኖረኝ የፈለኩትን ያንን ነገር ስሰጥ ነው፡፡

የምትፈልጉትን ነገር ለመስጠት እንደተፈተናችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ልጁን እንዴት እንደሰጠን ባሰባችሁ ጊዜ ራሳችሁን ጭምር እንኳን ስለመስጠት አታስቡም?

ይህ ቀላል እውነት ነው ፡- ደስተኛ ለመሆን መስጠት አለብን ፤ መስጠት ደግሞ እውነተኛ መስጠት የሚሆነው መስጠት ዋጋ ሲያስከፍለን ነው፡፡

 


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ስጦታዬ ትርጉም ያለው እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ ለመርዳት ይሁን ለመባረክ መቼ እና ምን መስጠት እንዳለብኝ ተናገረኝ፡፡ አንተ ፍቅርህን እንደሰጠኸኝ እኔም ለሌሎች መስጠት እፈልጋሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon