መቀበያህን ከአታላይ ነጻ አድርግ

ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤በየማለዳው ያነቃኛል፤በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል። ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም። (ኢሳይያስ 50:4-5)

ከእግዚአብሔር መስማት የመጀመሪያ እርምጃው ከእርሱ መስማት እንደምንችል ማመን ነው። ብዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር መስማት ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን በእርግጥ ከእርሱ ለመስማት አይጠባበቁም። “እኔ በቃ ከእግዚአብሔር መስማት አልችልም፤ በፍጹም አይናግረኝም።” ይላሉ።

እነዚህ ሰዎች እርሱን በግልፅ ለመስማት በ “በመቀበያዎቻቸው” ውስጥ በጣም ብዙ ጫጫታ አላቸው። ከክፉ ምንጮች በሚመጡ በጣም ብዙ መልእክቶች ጆሮዎቻቸው ተጨናንቀዋል። ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር በእርግጥ ምን እንደሚናገራቸው ለማወቅ ይቸገራሉ።

ከእርሱ እየሰማን እንደ ሆነ ካላመንን እግዚአብሔር ለእኛ መናገሩ ምንም አይጠቅመውም። አታላዩ ዲያቢሎስ ከእግዚአብሔር መስማት እንደምንችል እንድናስብ አይፈልግም። እኛ እንድናምን አይፈልግም ስለዚህም በዙሪያችን ቆመው ሌት ተቀን ከእግዚአብሔር መስማት እንደማንችል እንዲዋሹን ትንንሽ አጋንንትን ይልካል። እኛ ግን እንዲህ ብለን መልስ መስጠት እንችላለን፤ “እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፣ እግዚአብሔር እርሱን የመስማት እና የመታዘዝ ብቃት ሰጥቶኛል” (መዝሙር 40: 6 ን ተመልከት) ። የእግዚአብሔር ቃል ሁሉም አማኞች እግዚአብሔርን የመስማት እና የመታዘዝ እና በመንፈስ ቅዱስ የመመራት ብቃት እንዳላቸው ያውጃል።

ኢየሱስ ምን ጊዜም ከአብ በግልጽ ይሰማ ነበር። እግዚአብሔር በሚያናግርበት ጊዜ በኢየሱስ ዙሪያ ቆመው የነበሩ ብዙ ሰዎች ነጎድጓድ የመሰላቸውን ብቻ ይሰሙ ነበር (ዮሐንስ 12፡29ን ተመልከት) ። ከእግዚአብሔር መስማት ላይ ችግር ካጋጠመህ በየቀኑ ጥቂት ጊዜዎችን እንድትወስድ እና ከእርሱ መሰማት እንደምትችል እምነትህን እንድታውጅ እመክርሃለሁ። በልብህ የምታምነውን በምታውጅበት ጊዜ አእምሮህ ይታደሳል ደግሞም ከእግዚአብሔር ለመስማት መጠባበቅ ትጀምራለህ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ከእግዚአብሔር ለመስማት ውጥረት ውስጥ ከመሆን ይልቅ፣ እርሱ እንደሚናገርህ እመን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon