መናገርና መስማት

መናገርና መስማት

« …የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና»(መዝ.5፡2)።

ጸሎት በጣም ቀላል ነው፣ ወደ እግዚአብሔር ከመጸልና እርሱ ሊናገረን የሚፈልገውን ከመስማት የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ለመጸለይና ድምጹን በግል መንገድ እንድንሰማ ይፈልጋል።እርሱ እኛ ያለንበትን ሁኔታ በመቀብልና የእኛን ልዩ የሆነ የጸሎት መንፈስ እንድናገኝ በመርዳትና የራሳችንን የጸሎት ልምምድ በማጎልበት ከእርሱ ጋር ያለንን የግል ግንኙነት እንድናሳድግ ይፈልጋል። እርሱ ጸሎት ቀላል፣ የተለመደ፣ ከእርሱ ጋር ባለን ግንኙነት ህይወትን በሚሰጥ ግንኙነት ህይወታችንን ለእርሱ በማካፈልና እርሱም የልቡን ለእና እንዳካፍል እንፈቅዳለን።

እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚኖርን ሰው ከእርሱ ጋር በትክክል በተመሳሳይ መንገድ በጸሎት ግንኙነት እንዳደርጉ ለማድረግ በጣም ብዙ ነገሮችን ይሰራል። እርሱ ሁላችንም የተለያየን አድርጎ የሰራንና ባለን የተለያዩ ልዩነቶቻችን (ብዝሃነታችን) ያስደስተዋል። እኛ ሁላችንም ከእርሱ ጋር በምናደርገው መመላለስ በተለያዩ ሥፍራዎች የምንገኝ ነን። እና ሁላችንም በተለያዩ መንፈሳዊ ብስለቶች ላይ ያለን ነንና እንዲሁም እኛ ከእግዚአብሔር ጋር በተለየዩ ዓይነት ከእግዚአብሔር ጋር ልምምዶች አሉን። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበትና ድምጹን የመስማት ብቃታችን እያደገ ሲሄድና በቀጣይነት ለእግዚአብሔር እንዲህ ማለት ያስፈልገናል። «ጸሎትን አስተምረኝ፤ ካንተ ጋር መነጋገርና ከእኔ የተሻለ መንገድ ነው ባልኩት መንገድ አንተን መስማትእንድችል አስተምረኝ» በግሌ ያንተን ድምጽ ለመስማት እንድችል አስተምረኝ፣ እግዚአብሔር ሆይ እኔ ውጤታማ ጸሎት መጸለይ እንድችል ባንተ ላይ የምደገፍ ነኝና በጸሎት ካንተ ጋር ያለኝን ህብረት የበለጠገ፣ የህይወቴን ገጽታ የተባረከ አድርግልኝ።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ አንተ የእግዚአብሔር የተለየህ ፍጡር ነህ፣ በህይወትህና በጸሎት ህይወትህ ደስተኛ ሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon