መንገዱ ጠባብ ነው

መንገዱ ጠባብ ነው

ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ ፣ መንገዱም የቀጠነ ነውና ፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው፡፡ – ማቴዎስ 7፡14

እግዚአብሔርን መከተል ማት ‹‹በጠባብ መንገድ መራመድ›› ማለት ነው፡፡ አስቸጋሪ ነገሮችን መጋፈጥ ማለት ነው፡፡ የተማርኩት እና መንገዴን እንዳላቋርጥ ያደረገኙን ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. የእግዚአብሔር ቃል የሕይወቴ ድንበር ነው፡፡ በቃሉ በተሰመረልኝ ድንበር መሀል ውስጥ እስካለሁ ድረስ ማድረግ ያለብኝ እንዳደርግ ፣ እንዲኖረኝ የሚያስፈልገኝ እንዲኖረኝ የሚያደርግ በክርስቶስ ጥበብ እና ማስተዋል ይኖረኛል፡፡ እግዚአብሔር ለቃሉ ታማኝ እና እውነተኛ ነው፡፡
  2. የጀመርኩትን ለመጨረስ ፈቃደኛ መሆን አለብኝ፡፡ በስሜት የማይነዱ ሰዎችን ይጠቀምባቸዋል፡፡ በአዳዲስ ነገሮች መደሰት መልካም ነው ነገር ግን የተጀመረውን ነገር ዳር የሚያደርሱ ሰዎች በማያስደስት ጊዜ በጽናት እስከ መጨረሻ የሚደርሱ ናቸው፡፡
  3. የሚረዳኝ በሌለ ጊዜ በእርግጥ ኢየሱስ በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ የጠባቡ መንገድ ኑሮ እና ይህን ዓለም ባለመምስል የሚኖር ኑሮ ብዙ ጊዜ የብቸኝነት ኑሮ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በምድር ላይ አቻ የሌለው እድል ከኢየሱስ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የማድረጊያ ወቅት ነው፡፡

ይህ እውነታዎች እኔን እንደረዱኝ እናንተንም ሊረዷችሁ እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡ ዘወትር ይህንን አስታውሱ ፤ ተቋውሞው ቢበረታም በጠባቡ መንገድ መጓዝ ሽልማት ያለው እና ሊሄዱበትም የሚገባ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ በጠባቡ መንገድ መጓዝ እሻለሁ በክርስቶስ ያለውን የሕይወት መንገድ ፡፡ በአንተ ድንበር ውስጥ ጠብቀኝ ፤ እስከመጨረሻ እንደጸና እንዴት መኖር እንዳለብኝ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon