መንገድ የሚመራን መሪ ያስፈልገናል

መንገድ የሚመራን መሪ ያስፈልገናል

«… ለዓለምና ለዘላለም ይህ አምላካችን ነው፥ እርሱም ለዘላለም ይመራናል» (መዝ.48፡14)።

በእያንዳንዱ ቀን የህይወታችን ጉዞ እግዚአብሔር የእና መሪ መሆኑን ማወቅ እጅግ ያስደስተኛል። አንድ አካል የሚመራን መሆኑን ማወቅ ምንኛ የሚያስደንቅ ነገር” “ነው፤ እንዲሁም ከአንዱ የህይወት መዳረሻ ወደ ቀጣይ እንደምትሻገር እርግጠኛ መሆንስ ምንኛ ያስደንቃል።

አንዳንድ ጊዜ እኔና ዴቭ ስንጓዝ፣ መገብኘት የምንፈልገውን ከሁሉም የተሻለውንና እጅግ ጠቃሚውን ሥፍራ እንዲያስጎበኝን አስጎብኚ እንቀጥራለን። አንድ ጊዜ አንዳንድ ሥፍራዎችን በራሳችን ብቻ ለመመልከት (ለመፈለግ) ወሰንን፣ በዚሁ ሁኔታ ያቀረብነው ምክንያት ማድረግ ያለብንን ማድረግ በምንፈልግበት ጊዜ ማድረግ እንድንችል የሚል ነበር። ይህንም እንጂ ይህ የመሰድነው የራስን መደገፍ ጉዞ ወደ መባከን አመጣን። ረጅሙን የቀኑን ጊዜ መንገድ ጠፍቶብን ያንን መንገድ መልሰን ለማግኘት ስንጥር ጊዜአችንን አሳለፍን። እኛም ከስህተታቸን ተምረን ለራሳችን ሥፍራ ፍለጋ ያለ ዓላማ ከመቅበዝበዝ ይልቅ አስጎብኚን መከተል ለእኛ
የተሻለ ሁኔታ ጊዜ መጠቀምን እንደሚሰጠን አወቅን።

ይህ የእኛ የጉዞ ሁኔታ ምሳሌ ለብዙ ሰዎች ህይወት ጋር የሚዛመድ ነገር አለው። በራሳችን የእኛ ካርታ እንፈልጋለን፡ የራሳችን መሪ መሆን እንሻለን እናም በሚመቸን ሁኔታ የራሳችንን የፈለግነውን ለማድረግ እንፈልጋለን። ነገር ግን እኛ በተለመደው የራሳችንን መንገድ ላይ እንከስራለን እንዲሁም ጊዜአችንም በመባከን ያልቃል። በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሄር በህይወታችን ሊመራን ተስፋ ቃል ሰጥቶናል፣ ይህንን ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ለእኛ በሚናገረንና ወደ ምንሄድበት መንገድ ሁሉ በሚናገረን በኩል ይሰራል፣ እንዲሁም እኛ እንዲመራን ከጠየቅነው እርሱ ምን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ በእያንዳንዱ የህወትህ ጊዜያት፣ እስከሞትም ጭምር፣ የትም ብትሆን እግዚአብሔር በዚያ አለ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon