እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወሰናቸው፤ይኸውም ከብዙ ወንድሞች መሀከል እርሱ በኩር እንዲሆን ነው፡፡ – ሮሜ 8፡29
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለእኛ ፍጹም የሆነ ሀጢያት አልባ መስዋዕት ለመሆን ነው ምክንያቱም እኛ በተፈጥሯዊ መንገድ ፍጹም የመሆን ችሎታ ስለሌለን ነው፡፡ከእርሱ መስዋዕትነት የተነሳ በየዕለቱ የበለጠ ኢየሱስን እንመስላለን፡፡ኢየሱስ እንደኖረው ስንኖር ደግሞ መንፈሳዊ ቅርሳችንን እንቀበላለን፡፡
እንደ ኢየሱስ የጽድቅ ኑሮን መኖር በአንድ ለሊት የሚመጣ ጉዳይ አይደለም እኛም አንችለውም፡፡ፍጹም ብንሆን ኖሮ አዳኝ ባላስፈለገንም ነበር! አሁንም መንፈሳዊ ቅርሳችንን ለማሟላት እና እና ለመደሰት በልባችን ልንሻ ይገባል፡፡ወደ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል እንደሚያሳድገን አውቀን እግዚአብሔርን መታመን ልንማር ይገባናል፡፡
ኤፌሶን 1፡11-12 ሲናገር እንደእርሱ እቅድ አስቀድሞ የተወሰንን እኛ …በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው!
ርስት አላችሁ እናም እግዚአብሔር ማን እንደሆናችሁ እና የማን እንደሆናችሁ ከማወቅ ከሚመነጭ የሰላም እና የደህንነት ስሜት ጋር እንድትኖሩ ይፈልጋል፡፡
በየዕለቱ ልጁን የበለጠ እየመሰላችሁ እንድትሄዱ በማድረግ እንዲቀይራችሁ እግዚአብሔርን ታምኑታላችሁ?
የጸሎት መጀመሪያ
በኢየሱስ ስላለኝ መንፈሳዊ ቅርስ አመሰግናለሁ፡፡በየዕለቱ ወደ ልጅህ መልክ እንደምትቀርጸኝ በማወቅ አመሰግናለሁ፡፡