እሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር? (ዘዳግም 32:30)
ከዚህ በፊት እንዳካፈልኳችሁ ሰዎችበዕለት ተዕለት ኑሯቸዉ ተስማምተዉ ለሚፀልዩት የስምምነት ፀሎት እግዚአብሔርመልስ ይሰጣል፡፡ለመስማማትና አንድነት ትልቅ ቦታ ለሚሰጡ ሰዎችን ይፈልጋል “በህብረት ስትሆኑ መንፈሴን በመካከላችሁ አፈሳለሁ” ያለዉ ቃል ይፈፀማል፡፡
ተመልከቱ፤ መስማማት ከፍተኛ ኃይልያለዉ የመደመር ሳይሆን የማባዛት መርህ ያለዉ ነዉ፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ለዚህ ነዉ አንድሰውሺህንሁለቱ ድግሞአሥሩንሺህያሸሻሉ የሚለዉ፡፡ ስምምነት የመደመር መርህ ላይ የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ አንዱ ሺዎቹን ሁለቱ ድግሞ ሁለት ሺዎቹን ያሸሹ ነበር፡፡ ነገር ግን ህብረት የእግዚአብሔርን በረከት ያዛል የእግዚአብሔር በረከት ደግሞ ብዜትን ያመጣል፡፡ ስለዚህ በእዉነተኛ ህብረት የሚደረግ ፀሎት በመንፈሳዊዉ አለም ጠንካራና ሁሉን ቻይ ኃይል ያለዉ ነዉ፡፡
ሥንከፋፈል ደካማ ህብረት ሲኖረን ደግሞ ጠንካራ እንሆናለን፡፡ በርግጥም ከኛ ጋር ያለዉ ኃይል ህብረታችንና አንድነታችንን ለመጠበቅ የሚረዳን ነዉ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ማድረግ ያለበትን ቢያደርግም ሆነ ባያደርግ የራሳችሁ ድረሻ ይኖራችኋል በዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ይባርካችኋል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ሁሉም ሰዎች እንዲስማሙ ማድረግ አትችሉም ነገር ግን እናንተን ከማናደድ ማስቆም ትችላላችሁ፡፡