መንፈሳዊ ጽናት

እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ። (1 ቆሮንቶስ 14:15)

በጽናት እንድትጸልዩ ፣ በልማዳዊና ድግግመሽ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በሆነ፣በጽናት የተሞላ ጸሎት እድትጸልዩ አበረታታችኋለሁ፡፡ ትርጉም የሌለዉ ጸሎት በአፋችን ማነብነብ እንችላለን፣ እንዲህ አይነቱ ጸሎት ግን የሞተ ነዉ፡፡ ስለአንድ ነገር ሳስብ ጌታ የጸለያቸዉን ጸሎቶች መጥቀስ እችላለሁ፣ ነገር ግን ይህ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለኔ የሚያመጣዉ ነገር አይኖርም፡፡ በቅንነትና ከልብ ብጸልይ ግን እግዚአብሔር ሰምቶ ስራዬን ይሰራል፡፡

በከንፈር ብቻ የሆነ ጸሎት ለእግዚአብሔርም ሆነ ለህይወታችን የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ስለአንድ ነገር ደግመን ደጋግመን ስንጸልይ ትርጉም በሌለዉ ልማድ ዉስጥ እንገባለን፡፡ ከዚህ ይልቅ በተሃድሶ እንድንጸልይ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራን መፍቀድ ይኖርብናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንድንጸልይ ጉልበትና ጽናትን ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን በራስ ጽናትና በመንፈስ- መር ጽናት መካከል ልዩነት አለ፡፡

በጸሎት ጊዜ የአንደበታችን ቃላትከልባችን የማይመነጩ ከሆነ ጉልበት አልባ ናቸዉ፡፡ ስንጸልይ በምንጸልየዉ ጉዳይ ላይ ትኩረታችንን አድርገን መሆን ይገባል፡፡ ልባችን ከእግዚአበሔር ርቆ እያለ የሸመደድናቸዉን ቃላት ብቻማነብነብ የለብንም፡፡

የጻድቅሰውጸሎትበሥራዋእጅግኃይልታደርጋለች። (ያዕቆብ 5:16 ን ተመልከቱ) ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ወደ እግዚአብሔር ከልብ የምትጸልየዉ ጸሎት ጉልበት አለዉ፤ እሱም ይሰማሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon