
ይህን ካለ በኋላም፣እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤ – ዮሀ 20፡22
እግዚአብሔር የይቅርታን ልብ ይዘን እንድንኖር ይፈልጋል፡፡እኛ ሁላችን ምንም ያህል ዲያብሎስ አስተሳሰባቸችንን በመራርነት ለመመረዝ ቢጥርም በፈቃደኝነት እግዚአብሔርን ለመታዘዝ መርጠን ማናቸውንም በደል ከትንሽ እስከ ትልቅ ይቅር ማለት አለብን፡፡ብዙ ጊዜ ይሄንን ማለት ከማድረግ ይልቅ ቀላል ነው ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻችሁን እንድታደርጉት አልተዋችሁም፡፡
ያለ መንፈስ ቅዱስ ሀይል ይቅር ማለት አትችሉም፡፡በራሳቸሁ ለማድረግ እጅግ ከባድ ነው ነገር ግን በእውነት ፈቃደኛ ከሆናችሁ እንዲረዳችሁ መንፈስ ቅዱስን ይልካል፡፡ማድረግ ያለባችሁ በትህትና ለእርዳታ መጮህ ብቻ ነው፡፡
በዮሀ.20፡22 ላይ ኢየሱስ “እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤መንፈስ ቅዱስን ተቀበይ!” ቀጣዩ ትዕዛዙ ሰዎችን ይቅር ስለማለት ነበር፡፡
ለእናንተም የሚለው ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡በመንፈስ ቅዱስ ሞልቷችሁ ይቅር ለማለት የምትችሉ ሊያደርጋችሁ ይፈልጋል፤ነገር ግን ጠይቃችሁ ልትቀበሉት ይገባል፡፡እናንተ ፈቃደኛ ከሆናችሁ በልባችሁ ያለውን ማናቸውንም አይነት መራርነት እና ይቅር አለማለት ማስወገጃ ሀይል ይሰጣችኋል፡፡
እግዚአብሔርን የጎዷችሁን ሰዎች ይቅር ትሉ ዘንድ መንፈስ ቅዱስን እፍ እንዲልባችሁ ጠይቁት፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ፈቃደኛ ነኝ እፍ በልብኝና በመንፈስህ ሙላኝ፡፡የሚያስችለውን የመንፈስ ቅዱስን ሀይል ለመቀበል እና ይቅር ለማለት መርጫለሁ፡፡