መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳችን ይናገራል

«… እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል» (ዮሐ.16፡8)።

መንፈስ ቅዱስ በኃጢአታችን ሊወቅሰንና ስለጽድቃችን ሊያሳምነን ለመንፈሳችን ይናገራል። የእርሱ ወቀሳ ዓላማ ለንስሃ ሊያሳምነን ነው ይህም በተሳሳተ አቅጣጫ አሁን እየሄድንበት ካለንበት ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ ለመመለስና ለመጓዝ ነው።

ወቀሳ ማለት ሙሉ በሙሉ ከኩነኔ የተለየ ነው። ይህን ነገርለመማር ብዙ ጊዜያት ወስዶብኛልና በውጤቱ እኔ በተሳሳተ መንገድ መንፈስ ቅዱስ በህይወቴ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ባለተስማማሁበት አንድ ጉዳይ ል ሲወቅሰኝ ራሴን ስኮንን ነበር። ወቀሳ ከአንድ ነገር ውስት የሚያወጣን ማለት ነው። በህይወታችን ውስጥ ስላለው ዕቅድና ፈቃድ ወደ ል ከፍ የማደርገን ማለት ነው። በሌላ በኩል ኩነኔ ግን ወደ ታች የሚቀብርና ከጸጸት ሸክም ሥር የሚያውለን ማለት ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ በኃጢአታችን ሲወቅሰን የሚሰማን ሃፍረትና ጸጸት የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ንስሃ በገባንበት ኃጢአት በቀጣይነት ጸጸት የሚሰማን ከሆነ ግን ይህ ጤነኝነት አይደለም፣ የእግዚአብሔርም ፈቃድ አይደለም። በአመንዝራነት ኃጢአት ስለተያዘቸው ሴት ታሪክ ላይ (ዮሐ.8፡3-11) ኢየሱስ ያረጋገጠው ነገር ኩነኔ ወደ ሞት ብቻ የሚያመራ ይሆናል። ነገር ግን ወቀሳ ከኃጢአት ወጥተን አዲስ ህይወት ለመኖር እንድንችል የሚታደገን ነው።

እግዚአብሔር የሚኮነነን አምላክ ስላይደለ፣ ያለፍርሃት እንዲህ ብለን እንጸልያለን «ጌታ ሆይ ኃጢአቴን አሳየኝ፣ እኔ የሰራሁትን ማናቸውንም ሌሎችን መውደድ ያለብኝን የአንተን ህግ የጣስኩበትን ኃጢአት ውቀሰኝ ወይም ያንተን ፈቃድ እንዳላደርግ የሚከለክለኝን ውቀሰኝ። ህሊናዬን ለአንተ ድምጽ እንዲፈራህ አድርገኝ። ከኃጢአት ነጻ እንድሆን ሃይልን ስጠኝ። አሜን» በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ መኖር በህይወትታችን ለእግዚአብሔር ድምጽ የነቃን ሆነን ለመኖር ንቃታችንን ይጨምራል።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ሰይጣን ይኮንናል፣ መንፈስ ቅዱስ ይወቅሳል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon