ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፡፡ – ዮሐ 14፡16
የእኛ ቁጥር አንድ ጠላታችን ስሜቶቻችን ናቸዉ፡፡ በሚሰማን ስሜት የመመራት አዝማሚያ አለን ነገር ግን ስሜቶች ተለዋዋጭና ከቀን ቀን የሚቀየሩ መሆናቸዉን ልብ ማለት አለብን፡፡ ወደ አእምሮአችን የሚመጣዉን እያንዳንዱን ሀሳብ ላለመከተል ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ምክንያቱም አስተሳሰባችንና ስሜቶቻችን እዉነቱን አይነግሩንምና፡፡
ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ድብርት ዉስጥ የሚገቡት እዉነቱን ስለማይጋፈጡ ነዉ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የመጣዉ እዉነቱን ሊገልጥልን ነዉ፡፡ ዘወትር ማመካኘትና በሌሎች ማሳበብን ትተን እዉነቱን መጋፈጥና ስለድርጊቶቻችን ሀላፊነት መዉሰድ አለብን፡፡ ይህንን ስናደርግና እግዚአብሔርን እርዳታ ስንጠይቅ የከበደን መንፈስ ይለቀንና ነጻነትና ቅለት ይሰማናል፡፡
መንፈስ ቅዱስ ጋር በመስማማትና እርሱ የሚሰጥህን ጥበብ በመታዘዝ በስሜቶችህ ላይ ድል ማግኘት ትችላለህ፡፡ ኢየሱስ እርሱን የላከዉ አጽናኛችን፣ አማካሪያችን፣ አጋዣችን፣ አማላጃችን፣ ጠበቃችን፣ ሐይላችንና ሁሌ አብሮን እንዲኖር ነዉ፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን ቅር መሰኘት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ መከፋት፣ መደበር የለብንም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በስሜቶቻችን ላይ ድል ይሰጠናል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
መንፈስ ቅዱስ ስሜቶቼንና ባህርዮን በራሴ መቆጣጠር አልችልም፤ ወደ ድል የሚመራኝን ኀይልህን ስለምትሰጠኝ አመሰግንሃለሁ፡፡