መንፈስ ቅዱስ ከመስራት ወደ መሆን ያምጣችሁ

መንፈስ ቅዱስ ከመስራት ወደ መሆን ያምጣችሁ

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ። – ሐዋሥ 1፡8

በመጀመሪያዎቹ የዳግም ልደት ባገኘሁባቸው ወቅቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ አገልግሎቶች ብሳተፍም በችግሮቼ ላይ ድልን አላገኘሁም ነበር፡፡ ሌሎች ክርስቲያኖች የሚያድረጉትን ብመስል ደስተኛ የምሆን ይመስለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ብቻ በቂ አልነበርም ይልቁንም ውስጤ ሊቀየር ይገባው ነበር፡፡

ሐሥ 1፡8 የእግዚያብሔርን ኃይል የእርሱ ምስክር ለመሆን እንደተቀበልን ይናገራል፡፡ መገንዘብ ያለብን ምስክር ለመሆን እንጂ ምስክር ለመስራት ወይም ለማድረግ አይደለም፡፡ ማድረግ ከመሆን የተለየ ነገር ነው፡፡ የላይኛውን ሰውነቴን አሳምሬው ይሆናል ውስጠኛው ግን ደካማ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ቀን የውስጥ ማንነቴ ፈንድቶ ሲወጣ ሁሉም ሰው ከውጭ እንዳየኝ እንዳልሆንኩ ያውቀል፡፡

ምስጋና ለእርሱ ይሁንና አሁን ከእግዚያብሄር ጋር ባለኝ ግንኙነት ከዚያ በላይ መንቀሳቀስ እንደሚገባኝ ተረድቻለሁ፡፡ ወደ እርሱ በፀሎት ጩኸቴን ሳሰማ ሊረዳኝና በኃይለኛ እጁ ሊዳስሰኝ መጣ መንፈሱንም አፈሰሰብኝ እርሱም በእውነት እግዚያብሔርን እንድወደው አደረገኝ ቃሉም ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ሆነብኝ፡፡ አሁን ማስመሰል አልችልም፡፡

ይህንን መንፈስ ቅዱስ እንድትቀበሉ አበረታታችኋለሁ፡፡ ከመስራት ወደ መሆን ያምጣችሁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከማድረግ ወደ መሆን የሚያመጣኝን ኃይል አስታጥቀኝ፤ ከመላው ማንነቴ አንተን መከተልና መውደድ እሻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon